በስቱትጋርት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት አገራቸው ላቀረበችላቸው ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለአጠቃላይ መልሶ ግንባታ እና ሰብዓዊ እርዳታ (National Cause) የሚውል የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ አገራችን ላቀረበችው ጥሪ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።
በዚሁ መሠረት ነዋሪነታቸው በጀርመን ሀገር በስቱትጋርት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮ-ብሪጅ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት አገራችን ላቀረበችላቸው የድጋፍ ጥሪ 9,000.00 ዩሮ በመለገስ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢትዮ-ብሪጅ የተሰኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ላደረጉት ድጋፍ ሚሲዮኑ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ፤ ሌሎች ማህበራት፤ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች በተመሳሳይ መልኩ ተሳትፏችሁን አጠናክራችሁ እንድቀጥሉ ኤምባሲው ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።
የቁርጥ ቀን ልጆች የአገር ፍቅር የሚገለፀው በተግባር ነው!