ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን በበርሊን የኢፌዲሪ ሚሲዮን በድምቀት ተከበረ
በየአመቱ አ.ኤ.አ ማርች 8 ቀን በዓለምአቀፍና በአገር ደረጃ የሚከበረው የሴቶች ቀን አ.ኤ.አ እሁድ ማርች 14 ቀን 2021 በበርሊን የኢፌዲሪ ሚሲዮን ከሚሸፍናቸው አገራት የተወጣጡ ምሁራን፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የሚሲዮኑ ሰራተኞች በተገኙበት በዙም ዌቢናር በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
በጀርመን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፣ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ብዙነህ፣ የስነ-ስርዓቱ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በአገራችን የሴቶችን መብት ማክበርና እኩል ተሳታፊ በማድረግ ደረጃ ብዙ የተሰራ ቢሆንም አሁን በቂ አንዳልሆነ እንስተዋል። በአገራችን በተበሰረው ለውጥ ማግስት መንግሰት በወሰደው እርምጃ የአገሪቱ ግማሽ የካቢኔ አባላት ሴቶችን በማድረግ እንዲሁም ሌሎች የኋላፊነት ቦታዎች ላይ ተሳትፏቸው እንዲጨምር በማድረግ አመርቂ ስራ ተስርቷል ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል በመሆናቸው ተሳትፏቸው እንዲጨምር ተገቢው ትኩረት ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላ በኩል በጀርመን እና ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸው አገራት የሚኖሩ ዳያስፖራ ምሁራን፣ ሙያተኞችና ታዋቂ ግለሰቦች በሴቶች ዙሪያ ያላቸውን አስተማሪ ገጠመኞች፣ የታዋቂ እና ተጽኖ ፈጣሪ ሴቶችን የህይወት ተሞክሮ፣ እንዲሁም የእራሳቸውን የህይወት ልምድ አካፍለዋል። የሙዚቃና ግጥም ስራዎች ቀርበዋል። The Ministry of Foreign Affairs of EthiopiaSpokesperson Office of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia#womensday2021