የበርሊን ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች በቀረበው አገራዊ ጥሪ መሰረት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለአጠቃላይ መልሶ ግንባታና ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ድጋፍ እንዲያደርጉ በቀረበው አገራዊ ጥሪ መሰረት የበርሊን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
ሰራተኞቹ ከመስከረም ወር ደሞወዛቸው በጥቅሉ 3570.40 ዩሮ በመለገስ በሀገር ቤት ለሀገራዊ ጥሪ/National Cause/ በተከፈተው አካውንት አስተላልፈዋል።
በጀርመንና አካባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለቀረበው አገራዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ድጋፋችሁን ለዚህ ዓላማ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ እንድትልኩ ጥሪ እናቀርባለን።