“የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛው ዉሃ ሙሌት መዳረሻ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በጀርመን በርሊን ተካሄደ ።
(ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ) “ለሕዳሴ ግድባች የቁርጠኝነት ሕዳሴ” በሚል መርህ ቃል የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛው ዉሃ ሙሌት መዳረሻ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በጀርመን በርሊን ተካሂዷል ።
ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን ፌ.ሪ.፣ በቼክ ሪፐብሊክ፣ ፣በፖላንድ ሪፐብሊክ ፣ በእስሎቫኪ ሪፐብሊክ እና በያዩክሬን የኢትዮጵያ ፌዲራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ ሀገራትና ከተሞች ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ጥሪ መሠረት በክብርት አምባሳደር መኖሪያ ቤት የሦስተኛው ዉሃ ሙሌት መዳረሻን በማስመልከት ቦንድ በመግዛት እና በስጦታ ተሣትፎ አድርገው ከ20,000 ዩሮ በላይ መሰብሰብ ተችሏል ።
በዝግጅቱ ክብርት አምባሳደር ሚሲዮኑ በሚሸፍናቸዉ ሀገራትና ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን በሁሉም ዘርፍ አገራቸዉን ስለሚደግፉና የኤምባሲውን ጥሪ ተቀብለው ለግድባችን ዘሬም አለን በማለት ለሰጡት አገራዊ ምላሽ አመስግነዉ ይሄ ዝግጅት የኢትዮጵያዉያን የአብሮነት ማሳያም ነዉ ብሏል።
በመድረኩ ላይ የዳያስፖራው አደረጃጀቶቹ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይና በሚሲዮኑ የአገልግሎት አሰጣጥ በማስመልከት ታዳሚዎቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ በመስጠት የተጀመረውን ሀገራዊ አንድነት በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል አገራቸውን መደገፍ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል::