Embassy of The Federal Democratic Republic of Ethiopia in Berlin
  • Home
  • Notice
  • About us
    • Staff
    • Holidays
  • Visit Ethiopia
    • Geography
    • Population
    • History
    • Climate
    • Calendar
  • Consular Services
    • Diaspora and Consular Affairs Section
    • የቆንስላ አገልግሎት
    • በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ
    • Consular
    • Further Services
    • Konsularische Dienstleistungen
    • Visa
  • Contact

የዓድዋ በዓል አከባበር

Mar 3, 2023

የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በኤምባሲያችን የዓድዋ ድል በዓል ተከብሯል፡፡ በእለቱም ክቡር አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ፣ በበርሊን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ምከትል የሚሲዮን መሪና ጉዳይ ፈጻሚ እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ በመቀጠልም አድዋ አያቶቻችን ከደቡብ እሰከ ሰሜን፣ ከምሥራቅ እሰከምእራብ በአንድነት ተሰባስበው ድል የተቀዳጁበት መሆኑንና አገራችን ኢትዮጵያን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩን መሆኑን፣የአስተሳሰብ ልእልናችንን ያሳየንበት፣ በቅኝ አገዛዝ ሥር የወደቁ ለትግል መነሻ ያደረጉበት ጭምር እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ስለዚህም የአድዋ ድል የአለም ታሪክን የለወጠ መሆኑን በማንሳት ቀጥሎም ከኤምባሲው ሠራተኞች ጋር በዓሉን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም አድዋ ከዲፕሎማሲ ሥራችን ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን ለአብነት ያክል የውጫሌ ውልን በማንሳት እንዲሁም አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም መነሻ መሆኑንና ከአድዋ በመነሳት ያሉብንን ችግሮች በኛ ዘመን የምንሻገርበት ማድረግ እንደሚገባ ተንጸባርቋል፡፡

ቀጥሎም ማምሻውን በበርሊን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በተወከልንባቸው አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በዙም የዓድዋ በዓል ተከብሯል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይም ክቡር አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ የሚሲዮኑ ምክትል መሪና ጉዳይ ፈጻሚ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በዓሉን የከፈቱ ሲሆን፣ ለ127 ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ በዓል “ለአገራዊ አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት መልህቅ” በሚል መርህ በጋራ ለማክበር በመቻላችን ትልቅ ክብር ይሰማናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለአድዋ ድል ላበቁን አያቶቻችን ክብርና የድሉን ቀን የምናከብርበት አንድ ሆነን ሁላችንም በእኩልነት ለአገራችን የምንሰራበት ቁርጠኛ ሆነን የምንቆምበት እንዲሁም መስዋእትነት ለመክፈል ትምህርት የምንወስድበት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ላቀ አስተሳሰብና አመለካከት በአንድነት መሻገር ይገባናል ሲሉም አሰምረውበታል፡፡

በእለቱም ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በክብር እንግድነት በመገኘት በዓሉን አስመልክቶ ገለጻ የሰጡ ሲሆን፣ቀስቃሽ ግጥምና ፎከራዎችን አሰምተዋል፣ ከታዳሚዎች ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ መልስ የተሰጠበት ሲሆን፣ የእለቱን ፕሮግራም ክቡር አምሳሳደር ተፈሪ ታደሰ ማጠቃለያ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

 

Related Posts

Invitation of Investment Forum in Addis Ababa, Ethiopia, from April 26-28, 2023

News /

Invitation of Investment Forum in Addis Ababa, Ethiopia, from April 26-28, 2023

በጀርመን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በርሊን ገቡ

News /

በጀርመን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በርሊን ገቡ

Statement on the “Resolution” of the League of Arab States Regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) #Ethiopia

News /

Statement on the “Resolution” of the League of Arab States Regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) #Ethiopia

‹ ማስታወቂያ / Notice › የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ Twin Cities World Tourim Forum ፎረም ላይ ተሳተፉ

Visa , passport and ID request Link

Use the following link to obtain service without a Diplomatic visa.

Apply for a Visa Online:  http://www.evisa.gov.et/

Apply for Passport & Ethiopian-Origin ID Card online:  http://www.digitalinvea.com/

Latest Post

  • Invitation of Investment Forum in Addis Ababa, Ethiopia, from April 26-28, 2023
  • በጀርመን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በርሊን ገቡ
  • PRESS RELEASE
  • የጋብቻ ማስታወቂያ

Improtanat Consular Contacts

በሚሲዮን ለሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚከተሉትን የስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይቻላል፡፡

  1. በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስልክ ኦፕሬተር ቁጥር +4930772060

የቆንስላ ጉዳዮችን በሚመለከት ለሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. ሰነድ አልባ ፣ፓስፖርት ፣ ፓስፖርት ይፈለግልኝ ፣ የትውልድ መታወቂያ

          ሀ. አቶ አሻግሬ ሀብታሙ +4915218016085

           ለ. ወ/ሮ ሽኩሪያ ዴታሞ  +49307720612

  1. ሰነድ ማረጋገጥ ፣ውክልና ፣ ወሳኝኩነት ማለትም /ጋብቻ/ ፣ ሊሴፓሴ ፣ ወደ አገር ቤት ለሚሄዱ የድጋፍ ደብዳቤዎች መስጠት ፣ ወደ አገር ቤት ለሚላክ አስከሬን የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት

            አቶ ተክላይ መዝገበ +493077206142

           Email: teklay.mezgebu@mfa.gov.et

  1. ዲያስፖራ አካውንት መክፈት ፣ሞርጌጅ /በብድር ቤት መግዛት/ ፣ የቦንድ ሽያጭን በተመለከተ ፣ ወደ አገር ጠቅልለው ለሚገቡ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት ፣ የኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ኮሚኒቲ ማደራጀት ፣ ኢንቨስትመትን በተመለከተ /ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሆኑ/

             ወ/ሮ ሰብለ ቱሉ +49307720615

             Email:  seble.dadi@mfa.gov.et

  1. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች

           +49307720616

Facebook

Ethiopian Embassy in Germany

Twitter

Follow @ethioingermany

Back to Top

Consular Service

Monday, Tuesday and Thursday
Morning 8:30 -12:30
Afternoon 13:30 – 17:30

The Embassy remains closed on German and Ethiopian holidays.

Working Hours:

Monday to Friday.
08:30 to 12:30 and 13:30 to 17:30

Address

Boothstrasse 20a, 12207 Berlin, Germany

  • About us
© Embassy of The Federal Democratic Republic of Ethiopia in Berlin 2023