የጀርመን መንግሥት በበርሊን አዲስ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ክብርት አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ ተናገሩ
(ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ): የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ይህን ያሉት በበርሊን አዲስ የሚገነባዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ሕንፃ የሚሰራበትን ቦታ በእርሳቸው ከሚመራው ልዑክ አባላት ጋር በመሆን ዛሬ በጎበኙበት ወቅት ነው።
በጉብኝቱ ወቅት በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተወካይ እና ህንፃውን በሚገነባው ሥራ ተቋራጭ ሀላፊዎች ስለ ህንጻው አሠራርና ጠቅላላ ሁኔታ ገለፃ ተደረጎላቸዋል። ስለ ሂደቱ ደግሞ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ ከጀርመን መንግስት በኩል ስለተደረገዉ ጥረት አመስግነዋል።
ክብርት አምባሳደር አዲስ የሚገነባው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት የሁለቱ ሀገራት መልካም ግንኙነት ማሳያ በመሆኑ ሕንጻውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።