Press Release on the Tripartite Meeting on the #GERD PRESS RELEASE ON THE TRIPARTITE MEETING OF MINISTERS OF FOREIGN AFFAIRS AND MINISTERS OF WATER AFFAIRS ON THE GERD Addis Ababa (03 January 2021)
The virtual meeting of Ministers of Foreign Affairs and Ministers of Water Affairs of Ethiopia, Egypt, and Sudan is held on 03 January 2021. The meeting is convened by the Minister of International Relations and Cooperation of the Republic of South Africa and Chairperson of the AU Executive Council.
The Ministers exchanged views on the continuation of the trilateral negotiation focusing on a draft document presented by the experts assigned by the Chairperson of the African Union. Ethiopia pronounced its positive outlook towards the draft document and expressed its willingness to use it as a single work document for the trilateral negotiation. Similarly, Sudan conveyed the importance of the document for the progress of the negotiation and its willingness to proceed with the negotiation with a defined role of the AU experts. Egypt categorically rejected the document.
Most of the issues on the first filling and annual operation of the GERD are agreed on. The main difference lies on the co-relations between the GERD Guidelines and Rules and the future water development projects on the Abbay Basin.
The GERD is a non-consumptive hydroelectric generating dam. Any agreement over the dam, which is being negotiated in the absence of a comprehensive water treaty and the prevalence of an unjust status-quo, shall be considerate of these fundamental factors. Ethiopia will not agree to a GERD deal that will in any way restrict its right to use the Nile waters.
On this basis, Ethiopia is committed to conclude the negotiation with good faith to reach an agreement. Accordingly, Ethiopia forwarded alternative approaches to Egypt and Sudan, which is hoped to garner their affirmative response.
In the coming week, the trilateral meetings will continue at expert’s level with oversight of ministers of water affairs, to take stock of agreed and outstanding issues to be presented to the six ministers meeting that is expected to be held on Sunday the 10th of January 2021.
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ
የፕሬስ መግለጫ
አዲስ አበባ (ታሕሳስ 25 ቀን 2013 )
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል። ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል።
ሚኒስትሮቹ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ያደረጉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ በማተኮር ምክክር ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረጹትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው እና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን ገልጣለች፡፡ የሱዳን ወገን በበኩሉ ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ላይ ቢጋር በማጽደቅ ድርድሩን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው ገልጧል፡፡
የሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና ዓመታዊ አስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት ቢሆንም፣ ወደፊት በዓባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የውሃ ልማት ሥራዎች ጋር የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሃሳብ ነው፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍጆታ የሌለው የኃይል ማመንጫ ግድብ እንደመሆኑ በግድቡ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ይህንኑ ከግምት ያስገባ እና የተሟላ የውሃ ስምምነት በሌለበት እና ኢፍትሃዊ አጠቃቀም በሰፈነበት ተፋሰስ የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን ኢትዮጵያ አትፈቅድም፡፡
ይህን መሰረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ አሞላል እና ዓመታዊ አስተደዳር የሚመለከተውን ደንብ በጋራ ስምምነት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ናት፡፡ በዚህም መሰረት የስምምነት አማራጮችን ለግብጽ እና ሱዳን ወገን ያቀረበች ሲሆን የሃገራቱ ምላሽ ቀና እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል፡፡
በቀጣይ የሃገራቱ ባለሙያዎች በውሃ ሚኒስትሮች አመራር ስር ስብሰባቸውን በመቀጠል ስምምነት የተደረሰባቸውን እና የልዩነት ሃሳቦችን በመለየት በቀጣይ ዕሁድ ጥር 01 ቀን 2013 ለሚካሄደው የስድስት ሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤቱን ያቀርባሉ፡፡
The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
Office of the Prime Minister-Ethiopia