ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን የሙኒክ ቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ጎበኙ
በጀርመን የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ ክብርት ሙሉ ሰለሞን የሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲን በጎበኙበት ውቅት፣ ለግብርና ምርት ጠቃሚ የሆነ፣ በሙኒክ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ፣አውቶሞቲቨ ዲፓርትመንት ጥናት መስረት ፣ በዩኒቨርሲቲው እና በግል ድርጅት የተመረቱትን
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች ፣ ቢስክሌት፣ እንዲሁም አውቶማቲክ ( ሾፌር አልባ) መኪኖች ፣ መረጃ መስብስቢያ በጣም ትንሽ መሣሪያ፣stimulation፣ የኤሌክትሪክ መጠንና ሌሎች ጉዳዮችንም መመርመሪያ መሳሪያ፣ ወዘተ ማየትና ገለፃ ማግኘት ችለዋል።
የመኪኖቹን ናሙና የሙኒክ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተተገበረ ሲሆን፣ ጉብኝቱ በኮሮና ምክንያት ቢዘገይም ፣ ናሙናው በተጠናቀቀበት ውቅት በመሆኑ ፣ ጥሩ አጋጣሚ ነበር ።
ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ፤ ምርትን ገበሬው ወደ ገበያ የሚያጓጉዝበት ፣ የአየር ንብረቱን ያገናዘበ በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ እንዲመረት፣ ተገቢ ሙያዊ ድጋፍ እና ሥልጠና ለመስጠት ተስማምተዋል።
የመስክ ጉብኝቱ እንዳለቀ ከሀላፊዎች ጋር ውይይት ተድርጎ፣ ሰለ ወደፊት የጋራና የትብብር ስራ አቅጣጫ ምክክር ተደርጓል።
በሙኒክ የኢትዮዽያ የክብር ኮንሱል ወ/ሮ ማክሲሚላኒያ ሹለርም
(Mrs.MaximilinaSchürrle) በጉብኝቱ እና በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።
ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የግብርና ምርት ማጓጓዣ መኪኖች በGIZ ድጋፍ ወደ ሀገራችን የተጫኑ ሲሆን ፣በቅርቡ
እንደሚገቡ ተረጋግጧል።
ክብርት እምባሳደር ሙሉ ሠሎሞን በተለያየ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ላለው ጥናትና ምርምር፣በኮሮና ውሳኝ ወቅት ለየኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ ላበረከተው ድጋፍ እመስግነዋል።