
About Public Diplomacy
Posts by Public Diplomacy:


ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን “Women Energize Women” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው Energy Transition ፓነል ላይ ውይይት አደረጉ
በጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮችና ክላይሜት አክሽን ትብብር ሚኒስቴር ( German Federal Ministry of Economy and Climate Acion) እና በአፍሪካ ፈራየን ( Africka Verein – German Africa Business Association) እ.ኤ.አ ጁን 03/2022 በጋራ በተዘጋጀው ፓነል ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ብዙነህ ፣በጀርመን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር “Women Energize Women” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ፓነል በተናጋሪነት እና በክብር እንግድነት የተጋበዙ ሲሆን፣ በፓነሉም ስለሃይል ሽግግር፣ ስለታዳሽ ኃይል፣ የሃይል እጥረት መፍትሔ ወይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህም የሴቶች ተሳትፎ ምን ይመስላል የሚለውም ተነስቷል፡፡ በፓነሉ አዘጋጆች ለመነሻነትም በአሁኑ ግዜ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኮሮና ወረርሽና የሃይል እጥረትን ጨምሮ የተስተዋሉ በአለም ላይ ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በውይይቱም ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በአሁኑ ሰዓት የኤለክትሪክ ተጠቃሚነት በኢትዮጵያና በሌሎች የአለም አገሮች ጭምሮ አናሳ መሆኑን ጠቅሰው ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከውሃ ፣ ከነፋስ ፣ ከፀሐይ፣ ወዘተ የሚገኝ የኤሌትሪክ እና የሃይድሮጅን ሀይል የማመንጨት እምቅ ሀብት ቢኖራትም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አምስት በመቶ ብቻ ንጹህ የምግብ ማብሠያ ሀይል ተደራሽነት ( Clean Cooking Accees) ያላት በመሆኑ ፣ በአብዛኛው ለምግብ ማብሠያ እንጨትና የተለያዩ ማገዶዎች (biomass) የሚጠቀሙ መሁኑን ገልጸዋል። ይህም ለጤናና ለከባቢ ምህዳር ( environment)ጠንቅ መሆኑን፣ አውስተው በአብዛኛው የቤተሠብ ምግብ የሚያበስሉት ሴቶች በመሆናቸው በማገዶ በጭስ በሚመጣ ጠንቅ ለዐይን እና ለጉሮር እንዲሁም ለመተንፈሻ አካል ይህመም እንደሚሠቃዩ ገልጽው ፣ የጉዳቱ አዙሪት በዚህ ሣያበቃ ለማገዶ ዛፍ ሰለሚቆርጡ ከባቢው ምክዳር እና አየር ንብርት ሥለሚጐዳና ያልተጠበቀ ዝናብና ጽርቅ ስለሚያስከትል ህዝቡን ለረሃብ አደጋ እንደሚያጋለጥ ጠቅሠዋል ።
ለዚህም ከሃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከካርቦን ብክለት ነጻ የሁነ ታዳሽ የሀይል አቅርቦት ለማግኘት ለሚሰሩ ስራዎች ሴቶች የበኩላቸውን ድርሻ ከወንዶች ጋር በጋራ ማበርከት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ አንዱ ሴቶችን ለአመራር ማብቃት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል የተደረገውን አበረታች ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሃብት የተሻሻለ የሃይል አቅርቦት እንዲገኝ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እየተገነባ መሆኑን አንስተው በሌሎችም የሃይል አቅርቦት አማራጮች ላይም በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ እምቅ የታዳሽ ኃይል ሃብት ያላት መሆኑን በኢትዮጵያና በአፍሪካ ባለው የህዝብ ብዛት በርካታ ገበያ መኖሩን እና የኢትዮጵያ መንግሥት ለሀይል(ለኢነርጅ) ሽግግር አዲስ ፖሊሲ በመቅረጽ ለኢንቨስተሮች አመቺ ሁኔታን በመፍጠር የቀረጥና የታክስ ማበረታቻ በማድረግ የሥራ ሂደቱንም ለኢንቨስተሮች ቀልጣፉ በማድረግ ላይ እየሠራ መሆኑን አስረድተው ለዚህም የጀርመን በለሀብቶች በዚህ ረገድ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ባለፈው እንደዘገብነው ከጀርመን መንግሥት ጋር በጋራ ለመሥራት ከተግባባንባቸው አንዱ የሀይል (Energy) ጉዳይ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን።
ክብርት አምባሳደር ሙሉ የኮረና ወረርሽኝ አለምን አንድ መንደር እንዲሆን ማስገደዱን እንደ አንድ ማሳያ በማንሳት ገልጸው አየር ንብረትንና ሀይል የማግኘት ጉዳይንም ችግሩ እኔ አይመለከትም ብሎ ማሠብ እንደማያስኬድ አሣስበው በጋራ ማሰብና መስራት እንደሚያስፈልግ ፣ አንዱ ጋ ያለው ችግር ለሌላውም አንደሚተርፍ ጠቅሰዋል፡፡ አፍሪካም እንደአህጉር ወቅቱ የሚሰጠውን እድልና የተሻለ አማራጭ በማሰብና በመጠቀም መስራት እንደሚያስፈልጋት አስገንዝበዋል፡፡ ከታሳታፊዎች ለቀረበላቸውም ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የእለቱን ኮንፍረንስ አርእስት “Women Energize Women” የሚለውን በብዙ መልኩ ለማሥረጽ አነቃቂ ግጥም በማቅረባቸው ተሳታፊው አድናቆቱን ገልጿል፡፡ በፓነሉም በአካልና በዙም በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

