ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከAmbassador Christoph Retzalff ጋር ተወያዩ
ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በዛሬው ቀን ከAmbassador Christoph Retzalff, Director for Sub-Saharan Africa and Sahel ጋር የትውውቅ ቀጠሮ በመያዝ በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት በመገኘት ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው ክቡር አምበሳደር ፍቃዱ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ እንዲሁም በሁለቱ አገሮች ያለው ጥሩ ግንኙነት በተለያዩ መስኮችም ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ዙሪያ መክረዋል፡፡
አምበሳደር ራትላፈ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ገልጸው በቆይታቸው የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አምባሳደር ፍቃዱ በጀርመን መንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ድጋፍ አመስግነዋል፡፡