ስዊድን በኢትዬጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ
በስዊድን ጎተንነበርግ ከተማ የኢትዩጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት በ “እኔስ ለሀገሬ” ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስተባባሪነት የኢትዩጵያ ፌ.ዼ.ሪ. ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሣደር ክብርት ሙሉ ሠሎሞን ብዙነህ በተገኙበት በ11/ 02/2014 ( እ.ኤ.አ በ21/10/ 2021 ) ከምሽቱ 2:30 – 4:00 ሰዓት በዊብነር ውይይት ተካሂዷል :: በዚህ ኘሮግራም የኮሚቴው ሊቀመንበር አቶ ዩናስ ጸጋዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ክብርት አምባሣደር ሙሉ ሠሎሞን ስለ ኢትዬጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ካብራሩ በኋላ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ስጥተዋል:: ተሣታፊዎች በሠጡት ባቀረቡት ጥያቄና በሠጡት አስተያየትና አገርን ለማዳን የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ከመግለጻቸውም በላይ ፣ ኢትዩጵያን ለማዳን ህዝቡን ከሞትና ከስቃይ ለመታደግ ያለማቋሪጥ የገንዘብ የማቴሪያል የሀሣብ አና በዲጂታል ሚዲያ ከፍተኛ ተሣትፎ በማድረግ ለመርዳት ቃል በመግባት የኢትዩጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን አረጋግጠዋል:: ይህንንም ቀደም ሲል ከኢትዩጵያ ኤምባሲ ቢርሊን ጋር በመመካከር በ “እኔስ ለሀገሬ” ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስተባባሪነት 23 /10/2021 ስዊዲሽ ክሮነር 54,250. — ( ሀምሣ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሣ) በሀገራችን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን ገቢ አድርገዋል:: ለዚህና ለቁርጠኝነታቸው የኢትዩጵያ ፌ.ዼ.ሪ. ኤምባሲ፣ በርሊን ከፍተኛ ምሥጋናውን ያቀርባል:: ________________________<>______________________