በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የችግኝ ተከላ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፣
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በርሊን ደፕሎማቶችና ሰራተኘች ከአራት አመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒሰቴር ዶ/ር አብይ አህመድ “አረንጓዴ አሻራ “ በሚል የተጀመረውን ዛፍ የመትከል እና አገርን አረንጓዴ የማልበስ እንቅስቃሴ በመደገፍ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በአምባሳደር መኖሪያ ቤት የችግኝ መትከል ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።
በቀደሙት ሶስት ዙሮች “በአረንጓዴ አሻራ “፡18 ቢሊዮን የሚደርሱ ችጅግኞች የተተከሉ ሲሆን በተከታታይ አራት አመታት 20 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል በተያዘው እቅድ መሰረት በዘንድሮ ክረምት 18 ቢሊዮን ችግኖች ለመትከል ፕሮግራም ተይዟል።
አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለአለም እያሳየ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል።
በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የችግኝ ተከላ ላለፉት ዓመታት በተከታታይ አካሂዶአል።