በበርሊን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን አከናወነ
በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞንና የኤምባሲው ባልደረቦች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአገራችን በመካሄድ ላይ ያለውን በአንድ ጀምበር የ200 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻን በመቀላቀል በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ መትከል ፕሮግራም ተካሂዷል። በዛሬው ዕለት 15 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በቀጣይ በአምባሳደሯ መኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጨማሪ ችግኞች እንደሚተከሉ ታሳቢ ተደርጓል።
The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
#EthiopiaLandofOrigin