በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተደረገ ውይይት ወቅት ውሳኔ ተላለፈ
በበርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ሰራተኞች ነሃሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በወቅታዊ የአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ አገራችን በአሁኑ ወቅት ላለችበት ሁኔታ በምን መልኩ አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚቻል ሃሳብ ከተንሸራሸረ በኃላ በርካታ ዝርዝር ተግባራትን ተከፋፍሎ ለመሥራትና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በድጋሚ በተቀሰቀሰው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአንድ ወር ሙሉ ደመወዛቸውን ድጋፍ የሚሆን መዋጮ ለማድረግ እንዲሁም ለኅዳሴ ግድብ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በስጦታ ለመለገሥና በተጨማሪ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገብተዋል።