በጀርመን ሀገር የMax Planck Society አንዱ ተቋም የሆነውና በስቱትጋርት ከተማ የሚገኘው Max Planck Institute for Solid State Research በቦን ከተማ ከሚገኘው ከMax Planck Institute for Radio Astronomy ጋር በመተባበር በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል የተለያዩ ይዘት ያላቸውን የምርምር ጆርናሎችና ሜጋዚኖች ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት አበረከተ።
የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በጀርመን የስቱትጋርት Max Planck Institute for Solid State Research ቤተመጽሐፍት በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ም/ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰን ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው ተወካዮች በተገኙበት የምርምር ጆርናሎችና ሜጋዚኖች ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት እንዲደርስ ተበርክተዋል።
የተበረከቱት ጆርናሎችና ሜጋዚኖች ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በተለይ ለፊዚክስና ኬሚስትሪ ዘርፍ እጅግ ተፈላጊ መሆናቸው ተገልጿል።
በእለቱ አምባሳደር ተፈሪ የቤተመጻሕፍቱ የሥራ ሓላፊዎችን ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው መጽሐፍቶቹ ለአብርሆት እንዲደርስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።