በጀርመን በእሽቱትጋርትና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ




በጀርመን በእሽቱትጋርትና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት በ24-09-2021 የኢትዮጵያ ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሣደር ክብርት ሙሉ ሰሎሞን በተገኙበት፡ ከእሽቱትጋርትና አካባቢው ኢትዮጵያ የኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ፣ውይይት ተካሂድዋል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታና ስላለው የሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግር፡ ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን የያዘ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።እንደዚሁም በኢትዮ ብሪጅ እሽቱትጋርት አስተባባሪነት፡ ባለፈው የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከእሽቱትጋርትና አካባቢው የኢትዮጵያ የኮሚዩኒቲ አባላት ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለኤምባሲው አስረክበዋ ።በተጨማሪ በእለቱ ለህዳሴ ግድብ የገንዘብ ስጦታ፣ የቦንድ ሽያጭ፡ ፣ ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ የሚሆን “ዝም ከምል ብዬ” የእመቤት መንግስቴ መፅሃፍና የህዳሴው ግድብ አስረኛ አመት መታሰቢያ መፅሄት ተሸጧል።የስብሰባው ተሣታፊዎች ለመንግሥት የውጭ ምንዛሪ ድጋፍ ያለማቋረጥ በየወሩ ገቢ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል::በአጠቃላይ በእለቱ ዩሮ 8400.==(ዩሮ ስምንት ሽህ አራት መቶ) በብር 453,684.– ( አራት መቶ ሀምሣ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሠማንያ አራት ብር) ገደማ ገቢ በመደረጉ ኤምባሲው ለአስተባባሪው ለኢትዮ ብሪጅ ማህበር አመራር እና ለአባላቱ ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።