ክቡርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን የባህልና ዲፕሎማሲ ማዕከል ተገኝተው ንግግር አደረጉ ።
የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በጀርመን የባህል እና ዲፕሎማሲ ማዕከል ( German Institution for Culture and Diplomacy ) በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮች እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ አድርገዋል።
በጀርመን፣ በቼክ ሪፐብሊክ፣ በፖላንድ ሪፐብሊክ ፣ በስሎቫክ ሪፐብሊክ፣ በዮክሬይን፣ የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በባህል እና ዲፕሎማሲ ማዕከሉ ተገኝተው ባደረጉት ገለጻ በወቅታዊ ጉዳይ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል አግባብ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የሰላም ሂደቱን መቀጠሏንና ሕዝቡ መሰረታዊ አገልግሎት እና ሰበአዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠንክራ እየሰራች መሆኑን ፣ ሕዳሴ ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያ አቋም ምንንም መጉዳት እንደማትፈልግና በመርህ ድንጋጌ መሠረት ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት እየሰራች እንደሆነ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ኢትዮጵያ በለውጥ መንገድ ላይ እንደሆነችና የተሻሻሉ ተመራጭ የሚያደርጋት የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ለታዳሚያኑ አብራርተዋል ።
ከዝግጅቱ በተጓዳኝ ክብርት አምባሳደር ከተቋሙ ሚዲያ ጋር በወቅታዊ ሁኔታ፣ በባህል ዲፕሌማሲ እንዲሁም በቱሪዝም ዙሪያ ኢንተርሺው አድርገዋል።