ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን እ.ኤ.አ. ከኦክቶነር 12-13 2022, በፍራንክፈርት በጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማኅበር በተጠራው 1st Africa Trade and Investment confrence እንዲሁም 2nd African forum on Vocational and Training & Education መድረክ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል።
በመድረኩ ላይ ከ31 የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉ ሚኒስትሮች፣የኢንቨስትመንት ሃላፊዎች ፣ባንኮች፣አምባሳደሮች እንዲሁም የንግድ ተቋማት ባለቤቶች የተገኙ ሲሆን፤ከሀገራችን ስድስት የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ሶስት በጀርመን የሚኖሩ ዳያስፖራ የንግድ ባለቤቶች ተገኝተዋል።መድረኩ ጀርመን አፍሪካ ስላላቸው ትብብርና በቀጣይ ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት የተለያዩ ፓናል ውይይቶች ተካሂዷል ።
በመድረኩ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ሴቶችና ንግድ በሚል መድረክ ላይ ሴቶችን የሚያበረታታ መልክት አስተላልፈዋል። ከመድረኩ ጎን ከፍራንክፈርት የንግድ ምክር ቤት Managing director Dr.Jürgen Ratzinger እነዲሁም Mr Michael T. Fuhrmann Director for International Trade for Africa and Middel East ጋር ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በመሩት የሀገራችን የንግድ ባለቤቶች፣ እንዲሁም የጀርመን ዴስክ አፊሰር እንዲሁም የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማኅበር የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ማኔጀር አስማው ኒታሪ በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።አብሮ ለመስራትና የጋራ ውይይት መድረኮችን ለመድረግ ተስማምተዋል።