በኢት/ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በውጭ የኢት/ ኤምባሲዎች በቆንስላዎች አገልግሎት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ እንዲችል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት ለመመዝገብ የምዝገባ አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 7/2010 ሥራ ላይ ውሏል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ በበርሊንና አካባቢ እንዲሁም ኤምባሲው የሚሸፍናቸው ቼክ ሪፑብሊክ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫክያና ዩክሬን የምትኖሩ ኢትጵያውያን የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺና የሞት ወሳኝ ኩነቶችን በኤምባሲያችን አማካይነት ማስመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ ከታች የተገለጹትን መስፈርቶች አንብባችሁ ማሟላታችሁን ካረጋገጣችሁ teklay.mezgebu@mfa.gov.et ላይ ስማችሁንና የምትመዘገቡትን የወሳኝ ኩነት ዓይነት በመግለጽ ቀጠሮ ማስያዝ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሳቢያ፡-አሁን የተጀመረው ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከዚህ በፊት የተከሰቱትን ኩነቶች አይመለከትም፡፡ ሙሉ መረጃውን ከዚህ በታች የተገለፀውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡:
- የልደትምዝገባ
በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ- ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
ቅድመ-ሁኔታዎች
- በሚሲዮኑ የልደት ወሳኝ ኩነት ለማስመዝገብ የሕፃኑ ወላጆች አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆን አለባቸው፡፡
- ልደት የሚመዘገበው በሕይወት ለተወለደ ወይንም በሕይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፡፡
- ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ምዝገባ አገልግሎት ፈላጊ ልደቱን ራሱ ማስመዝገብ አለበት፡፡
- 18 ዓመት ሳይሞላቸው ልጅ የወለዱ ወላጆች የልጃቸውን ልደት ለማስመዝገብ ሲቀርቡ ከሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ አስተዳደር ማንነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ተመዝጋቢ ወላጆቹን በሚመለከት ቦታ ላይ መረጃውን ካስሞላ በኃላ የወላጅ ፊርማ ቦታ ላይ ሰረዝ (-) ምልክት በማድረግ ይታለፋል፡፡
ደጋፊ ማስረጃዎች
- ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡
- የሕፃኑ አሳደሪ ወይም ተንከባካቢ ልጁን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የአስዳሪነት ወይም የተንከባካቢነት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት
- የጋብቻ ምዝገባ
ቅድመ-ሁኔታዎች
- ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈጻም ማስባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈጸም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለቆንስላ አገልግሎት ክብር መዝገብ ሹም ማስታወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የሚፈጻም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
- የቆንስላው የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግሥቱ ጋብቻው የሚፈጻምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል ወይም በሚሲዮኑ ዌብ ፔጅ ላይ ያሳውቃል፡፡
- ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጋብቻ መቃወሚያ በጽሑፍመቅረብአለበት፤መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችሉ ወላጆችና ተወላጆች፣አቃቤ ሕግ፣ አሳዳሪ ወይም የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚልሰው መሆን አለበት።
- የክብር መዝገብ ሹሙ በቀረበው የጋብቻ መቃወሚያ ላይ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ማሳወቅ አለበት፡፡
- ወንድም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም አይችለም።
- ጋብቻ ህግ በሚከለክላቸው የሥጋና የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
- ተጋቢዎች በፍርድ ቤት እንዳያገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ የተገኘ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹሙ ጋብቻውን አይመዘገብም፡፡
- ማንኛውም ጋብቻ በፌዴራል ወይንም የቤተሰብ ሕግ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- በባህል መሠረት የሚፈጻም ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይንም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሠረት የተፈጻመ መሆን አለበት፡፡
- አንዲት ሴት በብቸኝነት ለመኖር በህግ የተወሰነው ጊዜ ሳያልፍ ከሌላ ወንድ ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
- የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
- በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡
ደጋፊ ማስረጃዎች
- ጋብቻው የሚፈጻመው በሚኖሩበት አካባቢ ከሆነ የነዋሪነት ማስረጃ የተሰጠ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡
- የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለመቅረብ አለበት፡፡
- ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የሞተችበት/ባት ከሆነ የሞት ምስክር ወረቀት ካለመቅረብ አለበት፡፡
- ከ6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት 3 በ 4 ሳ.ሜ የሆነ የተጋቢዎች ፎቶግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
- በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ሥርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
- የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
- የፍቺ ምዝገባ
ቅድመ-ሁኔታዎች
- የተፋቺዎች መረጃ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ ላይ ተወስዶ ይመዘገባል፤ሆኖም ያልተሟላ መረጃ ሲኖር አስመዝጋቢዎች በተለያየ ጊዜ ቢመጡም ተጠይቆ ይሞላል፡፡
ደጋፊ ማስረጃዎች
- ፍቺው ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልጽ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
- ፍቺው የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ የፍቺ ልዩ ውክልና ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ ከሆነ የተሰጠው የጋብቻ ምስክር ወረቀት መመለስ አለበት፡፡
- የሞት ምዝገባ
ደጋፊ-ማስረጃዎች
- የሟች የነዋሪነት ወይም የመኖሪያ መታወቂያ ወይንም ፓስፖርት ወይንም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ወይንም የመኖሪያ ፍቃድ ካለመቅረብ አለበት፡፡
- አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለለፈበት ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂ ያማቅረብ አለበት፡፡
- ሞቱን የሚያስመዝግበው ፖሊስ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ/ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰብ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ መቅረብ አለበት፡፡
- የጊዜ ገደቡ ላለፈ የሞት ምዝገባ ስለሞቱ መከሰት የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ሞቱ የተከሰተው በውጭ አገር ዜጋ ላይ ከሆ ነከ ጤና ተቋም የተሰጠ የሞት ማሳወቂያ ወረቀት ወይም ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡