የበርሊን ኤምባሲ ዲፕሎማቶኛና ሠራተኞች ለታላቁ ህዳሴ ግደብ ግንባታ የሚሆን የቦንድ ግዢና ስጦታ ፈፀሙ።
የበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዜጎቿ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደተጀመረ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግና የ3ኛ ዙር የውሀ ሙሌትና የ2ኛው ተርበይን ስራ መጀመርን በማስመልከት የ10,600 ዩሮ ቦንድ በመግዛት እና 600 ዩሮ ስጦታ በማድረግ በአጠቃላይ 11,200 ዩሮ ለህዳሴ ግደቡ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡