የአፍሪካ ቀን (Africa Day) በበርሊን ተከበረ
በበርሊን በአፍሪካ አምባሰደሮች ‘ግሩፕ’ አዘጋጅነት የአፍሪካ ቀን እ.ኤ.አ በ25/05/2022 በደማቅ ሁኔታ ተከበረ:: ለበዓሉ ዝግጅት ኢትዮጵያ ፣ በአፍሪካ አምባሣደሮች ዲን በሚመራው በዋናው አዘጋጅ ኮሚቴና በሌሎችም ኮሚቴዎች አባል በመሆን አገልግላለች።
ቀደም ሲል በ23/05/2022 የአፍሪካ ቀን ኮንፈረንስን በተመለከተ ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት ማገልገሏንና ውጤታማ ኮንፈረንስ መካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።
በበዓሉ ላይ ክቡር ብርሃም ክሊል (H.E. Brahim Killil ) በበርሊን የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን የሆኑት የሞሪታኒያ አምባሳደር እንዲሁም የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ዶ /ር አምባሳደር አክርማን በዓሉን በማስመልከት ንግግር አድርገዋል።
በበዓሉም ከፓርላማ፣ ከመንግስት መ/ቤቶች፣ ከኢንዱስትሪና ንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኃሳብ ቋት (think tanks ) ድርጅቶችና የተለያዩ ማህበራት መሪዎች እና አባላት ተገኝተዋል።
በዚሁ በ25/05/2022 በተከበረው በዓል ላይ የኢትዮጵያን የባሕል ምግቦች እና የኢትዮጵያን የቡና ሥርዓት በማቅረብ እንዲሁም ባህላዊ ልብስ በመልበስ በኤምባሲያችን አመርቂ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል። የቡና ስርዓታችንም ብቸኛና ልዩ ስለነበር የብዙ ተሳታፊዎችን ቀልብ መሳብ ችሏል