የጀርመን – አፍሪካ የሃይል (ኢነርጂ) ትስስር ጉባኤ በሀምቡርግ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል / German – African Energy Forum is underway in the city of Hamburg
የጀርመን – አፍሪካ የሃይል (ኢነርጂ) ትስስር ጉባኤ በሀምቡርግ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
15ኛው የጀርመን – አፍሪካ የሃይል (ኢነርጂ) ትስስር ጉባኤ ዛሬ በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በየዓመቱ እ.ኤ.አ በሰኔ ወር መግቢያ ላይ በጀርመን የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የግል ኩባንያዎች ጥምረት (አፍሪካ ፈራይን – Africa – Verein) እና በጀርመን መንግስት የኢኮኖሚ ጉዳዮችና አየር ንብረት (ከባቢ) ውሳኔ ሚኒስትሪ (Federal Ministry of Economic Affairs and Climate Action) የጋራ ትብብር የሚዘጋጀው ነው፡፡ የአፍሪካ ፈራይን በሀገረ ጀርመን በቀዳሚነት የሚቀመጡ 600 ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለሀብቶች በጋራ ጥምረት የተመሰረተ ነው፡፡ ጉባኤውን በይፋ የከፈቱት የጥምረቱ ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር ስቴፋን ሊቢንግ እና የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮችና ከባቢ ውሳኔ ሚኒስትሪ ተወካይ ናቸው፡፡
ይሕ ጉባኤ በዋናነት የአፍሪካ ሀገራት መሰረታቸው (ምንጫው) በሀገረ ጀርመን ከሆኑት የግሉ ዘርፍ ኩባንያዎች ጋር የትብብርና የድጋፍ ዕድሎችን በመፍጠር ከፍተኛ ሚና የሚጫወትና የሁለቱንም ዓለማት ሀገሮች በማቀራረብ የትስስርና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን የሚፈጥር ነው፡፡
በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በጉባኤው ላይ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ በጉባኤው የተሰጡ የመድረክ ዕድሎችን በመጠቀም ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የተሰጣትን የታዳሽ ሃይል አማራጮችን በማሳየት የጀርመን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የተመቻቸላቸውን እድል ጭምር አሰረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል ክቡር ሚንስትር ዴኤታው አትዮጵያ በተለምዶ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የውኃ ማማ ተብላ መጠራቷ አሁን ካለው እውነታ ጋር በፍጹም ትክክል እንዳልሆነና ለዚህም በቅርቡ እንደ ኦሮሚያና ሱማሌ ባሉ የአርብቶ አደር አካባቢዎች በተፈጠረው ድርቅና የዝናብ እጥረት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት ማለቃቸውን እንደማሳያ ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከ63 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሃይል አቅርቦት እንደሌላቸው በማንሳት ይኽም ትልቅ የሃይል ፍላጎት እንዳለና ለባለሀብቶቹ ትልቅ የገበያ እድል እንደሆነ ለጉባኤው አብራርተዋል፡፡
ይኽ ጉባኤ ጀርመን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የሃይል ሽግግር ዕቅድ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት በኢነርጂ ዘርፍ ያለውን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማሳደግና በመደገፍ ረገድ ጀርመን ከአውሮፓ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡ በጉባኤው ላይ እስከ 40 ሚደርሱ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች በጉባኤወ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
German – African Energy Forum is underway in the city of Hamburg
The 15th German – African Energy Forum is underway in the city of Hamburg. The forum is organized by the African – Verein in Collaboration with the German Ministry of Economic Affairs and Climate Action. Africa – Verein is an association of the first top 600 biggest companies in the energy sector in Germany.
Prof. Dr. Stefan Liebing officially opened the forum – Chairman of the Board of Directors and Delegate of the State Secretary of the Ministry of Economic Affairs and Climate Action. Ethiopia’s Delegation led by HE Dr. Sultan Woli – State Minister for the Energy sector has presented its challenges and opportunities in the energy sector during the plenary session with a dedicated topic on ‘Scaling up Investments and Partnerships for Renewable Energy in Africa’ hosted by the KONORAD ADENAUER STIFTUNG (KAS) on 1st of June 2022.
The plenary session, the state minister raised the wrong perception of Ethiopia’s being the water tower of Africa by showcasing the recent drought effect which is the direct cause for the death of hundreds of thousands of cattle in the pastoralist communities including Oromiya and Somali regions.
The delegation has also made strategic and meaningful bilateral meetings with both German Companies and Government officials. The meeting will continue until the 2nd of June with a good opportunity to bring together the African countries with German Private Business companies for partnership and attract investments. More than 40 African countries are attending the forum.