17ተኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል (የኢትዮጵያዊነት ቀን) ቀን በበርሊን ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተከበረ
17ተኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል (የኢትዮጵያዊነት ቀን) ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በበርሊን ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፤ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና የኤምባሲው ሰራተኞች በተገኙበት በዙም ተከብሯል።
ፕሮግራሙ በክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ፣ በቼክ ሪፐብሊከ፣ በስሎቫክ ሪፐብሊክ እና በዩክሬን ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ንግግር እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የተጀመረ ሲሆን፣ አምባሳደር ሙሉ በንግግራቸው የአገራችንን ሰላም ለማምጣት የሁላችንም አስተዋጽኦ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ሁላችንም እንደ ዜጋ ነገሮችን አይተን መርምረን ትክክለኛውን መረጃ ብቻ በማስተላለፍ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪ በሀገራችን ያለው የሀይማኖት የባህል እና የቋንቋ ብዝሃነታችን ውበታችን መሆኑን እና ኢትዮጵያ ግን ለሁላችንም አንድ መሆኗን ማመን እንዳለብን አስገንዝበዋል።
በመቀጠልም ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ምንነት እና ባህሪያት እንዲሁም የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በሚል ርዕስ ላይ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ገለጻ የቀረበ ሲሆን፣ በፌዴራሊዝም፣ በፌዴራል ፖለቲካ ስርዓት፣ በበህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ምንነት እና ባህርያት እንዲሁም በሃገራችን ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ላይ ማብራሪያ ተደረጓል።
ተሳታፊዎችም አስተያየት እና ጥያቄ በማቅረብ በውይይቱ እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን፣ በአምባሳደር ሙሉ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም በክብርት አምባሳደር ሙሉ መሪነት አንድነታችንን በሚያጠናክር በተደረገ ቃለ መሃላ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ፕሮግራሙ ተቋጭቷል።