
About Public Diplomacy
Posts by Public Diplomacy:


ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እና ክቡር አምባሳደር ፈቃዱ በየነ ከጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German-African Business Association Afrika-Verein ጋር ተወያዩ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመ አገር ከተካሄደው Berlin Energy Transition Dialogue.23 ተሣትፎ በተጨማሪም ከጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German-African Business Association Afrika-Verein/ CEO ከሆኑት Mr. Christoph Kannengiesser እና በኢነርጂ ዘርፍ ከተሰማሩ 14 የጀርመን ቢዝነስ ተቋማት ሓላፊዎችና ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ ክቡር ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነም የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German African Business Association Afrika-Verein/ ለአገራችን እያደረገ ላለው የተለያየ እገዛ በማመስገን ይኸው ድጋፍ በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር /German-African Business Association Afrika-Verein/ CEO የሆኑት Mr. Christoph Kannengiesser በበኩላቸው ኢትዮጵያ በድርጅታቸው ትኩረት ከሚሰጣቸው አገራት ግንባር ቀደም አገር መሆኗን በመግለፅ በሁሉም መስክ ድጋፍና ትብብራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር Africa-Verein ከሚያደርግው የተለያየ እገዛ በተጨማሪ በአገራችን በተለይም በኢነርጂ ዘርፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሰሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነም እ.አ.አ ኤፕሪል 26-28 2023 በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ “Invest and Grow in Ethiopia: The Land of Attractive Opportunities ” በሚል መርህ ቃል በሚዘጋጀው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እንዲሳተፉ በዉይይቱ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል ።

ክቡር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የኤምባሲውን ዲፕሎማቶች አወያዩ
የኢፌዲሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመን በርሊን ኤምባሲ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ውይይት አደረጉ። ክቡር ሚኒስትሩ በገለፃቸው ስለሃገራችን አጠቃላይ ወቅታዊ የልማ ት፣ የፀጥታ ፣የሰላምና የመልሶ ግንባታ ሂደት እና ታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በጀርመን የኢፌዲሪ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈቃዱ በየነ በበኩላቸው ሃገራችን እየሄደችበት ያለው የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት የበኩላችንን እንድንወጣ ጥሪ አድርገዋል።

የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቀረቡ
በጀርመን የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በዛሬው እለት በጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ምክትል ኃላፌ ለሆኑት Mr. Felix Schwarz የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቅርበዋል።
ክቡር አምባሳደር የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት የሁለቱን አገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን፣ ምክትል የኘሮቶኮል ኃላፊው በበኩላቸው ለክቡር አምባሳደሩ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ገልፀው ለስራቸው መቃናት አሰፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ጠቅሰዋል ።