
About Public Diplomacy
Posts by Public Diplomacy:

በጀርመን ፌ.ሪ. የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ጋር ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ብፁዕነታቸው ምዕመናኑን አስተባብረው ለተጎዱት በመድረስ እና በመደገፍ ሲያደርጉ ለነበረውና አሁንም ይሄንኑ የኤምባሲዉን ጥሪ ተቀብለዉ ስለተገኙ አምባሳደር ሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በውይይቱም ክብርት አምባሳደር በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ስላለዉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የአሸባሪዉ የህወሓት ቡድን ስላደረሰው ጥፋት እንዲሁም ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እየተደረገ ስላለዉ ጥረት እና በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት አገራችን የገጠማት ፈተና ለብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ አብራርተዋል።
ክብርት አምባሳደር በማያያዝም በአሁኑ ወቅትም በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ወገኖች ከአገራቸው ጎን እንዲቆሙ፣ የሚከፋፍሉንን በመተው እንደቀድሞ ሁሉ ለአንድነታችን ዘብ እንዲሆኑ አባታዊ ምክራቸውን ለምዕመናን ማድረስ እንዲቀጥሉና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመደገፍ ቤተክርስቲያኗ እንደከዚህ ቀደሙ አርአያነቷን እንድትቀጥል አምባሳደር ሙሉ ጠይቀዋል።
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በበኩላቸው የቤተክርስቲያኗን እና ምዕመናን በማስተባበር ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ክቡራን ተገልጋዮች የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ መስከረም 17 ቀን 2015 አግልግሎት የማይኖር መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
ክቡራን ተገልጋዮች የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ መስከረም 17 ቀን 2015 አግልግሎት የማይኖር መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
The Embassy is closed on Tuesday, September 27, 2022, on the occasion of the Founding of the True Cross ( Meskel Celebration).


የጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር ልዑካን የኢትዬጽያ ጉብኝት፤
ከጀርመን አፍሪካ የቢዝነስ ማኅበር የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ማኔጀር አስማው ኒታሪ አና በሚሲዮናችን መካከል በተደረገው ውይይይ መነሻነት ጀርመን ቆሻሻን ሰብስቦ መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ያላትን ሰፊ ተሞክሮ ወደ ሀገራችን ለማሰተላለፍ 14 አባላት የያዘ የቢዝነስ ልዑካን ሀገራችን ላይ ከ September 19-23 /2022, ጉብኝት አድርጎ ወደ ጀርመን ተመልሷል። በቆይታው የልዑካን ቡድኑ ክቡር አቶ እንዳለው መኰንን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ክብርት ፍሬ ነሽ መኩሪያ የአካባቢ ጥበቃ ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም በዘርፉ የሚሰሩ የግል ድርጅቶች በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። የጀርመን ኩባንያዎች በእውቀት፣ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ላቅ ያለ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል።