
News


ለሰብአዊ ድጋፍ ቃል መግቢያ መተግበሪያ


በጀርመን፣ በቼክ ፣ በፖላንድ ፣ በስሎቫክ እና በዩክሬን ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ኢትዮጵያ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ለገጠማት ፈተና፣የኢትዮጵያውያንን ስቃይ ለማስቆምና ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ በቁርጠኝነት መርዳት ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ያለውን የቃል መግቢያ መተግበሪያ ተጭናችሁ ልትረዱ የምትፈልጉትን የገንዘብ መጠን በመጻፍ ወይም ከሳጥኖች ውስጥ በመምረጥ ቃል መግባት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን። የቁርጥ ቀን ጥሪ ፣ ድጋፍ ቃል መግቢያ Link
www.eeb2015.net


ክቡርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በጀርመን ፌ.ሪ. የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ጋር ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ብፁዕነታቸው ምዕመናኑን አስተባብረው ለተጎዱት በመድረስ እና በመደገፍ ሲያደርጉ ለነበረውና አሁንም ይሄንኑ የኤምባሲዉን ጥሪ ተቀብለዉ ስለተገኙ አምባሳደር ሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በውይይቱም ክብርት አምባሳደር በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ስላለዉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የአሸባሪዉ የህወሓት ቡድን ስላደረሰው ጥፋት እንዲሁም ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እየተደረገ ስላለዉ ጥረት እና በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት አገራችን የገጠማት ፈተና ለብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ አብራርተዋል።
ክብርት አምባሳደር በማያያዝም በአሁኑ ወቅትም በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ወገኖች ከአገራቸው ጎን እንዲቆሙ፣ የሚከፋፍሉንን በመተው እንደቀድሞ ሁሉ ለአንድነታችን ዘብ እንዲሆኑ አባታዊ ምክራቸውን ለምዕመናን ማድረስ እንዲቀጥሉና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመደገፍ ቤተክርስቲያኗ እንደከዚህ ቀደሙ አርአያነቷን እንድትቀጥል አምባሳደር ሙሉ ጠይቀዋል።
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በበኩላቸው የቤተክርስቲያኗን እና ምዕመናን በማስተባበር ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
