በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የበርሊን ኤምባሲ የሚሰጥ የቆንስላ አገልግሎት
መግቢያ
-
ባለጉዳዮች ወደ በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኮንሱላር አገልግሎት በምትመጡበት ወቅት የተሟላ ሰነድ እና በቂ የሰነድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳወቅን ፣ ይህን በማሟላት ከመጣችሁ በኋላ ኮፒ ፍለጋ ላለመንከራተት እንዲሁም ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል፡፡
-
እንዲሁም መረጃዎቻችሁን በፖስታ የምትልኩ ባለጉዳዮች መረጃችሁን ወደ እናንተ መልሰን የምንልከው የመመለሻ ፖስታ ጨምራችሁ በምትልኩ ጊዜ ብቻ መሆኑን እናሳውቃልን፡፡
-
ከፌቡራሪ 2023 ጀምሮ የወጣው አዲስ የኮንሱላር አገልግሎት የዋጋ ታሪፍ
- በሚስዮኑ የቆንስላ ክፍል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ ዋና ዋና የአገልግሎት ዓይነት ሰነድ አልባ፣ቀድሞ የነበራቸውን ፓስፖርት ይፈለግልኝ ፣ የድጋፍ ደብዳቤ ፣ የሰነድ ማረጋገጥና የውክልና አገልግሎት ናቸው፡፡
- ከላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልግ ፎቶግራፍ ስፋቱ 3 x 4 ሴ.ሜ የሆነ፣ የሰውነት ክፍል በመቀስ ያልተነካ (ባዮሜትሪክ) ፣ ከስድስት ወር ወዲህ በከለር የተነሱት፣ ሁለቱ ጀሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለ፣ ከጀርባው ስም የተፃፈበት 4 ፎቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
- ለፓስፖርትና ለትውልድ ኢትዮጵያዊ የሚያስፈልግ አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲው መምጣት የማይችሉ የቼክ፣ ስሎቫክና ፖላንድ ነዋሪዎች በአካባቢዎ ለሚገኝ ፖሊስ አሻራውን በመስጠት በፓብሊክ ኖታሪና በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በማረጋገጥ መላክ ይኖርበታል፡
- ከዚህ ቀደም አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
- እድሜአቸው ከ 14 አመት በታች የሆኑ ህፃናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡
- አገልግሎቱን ለመውሰድ የሚያስፈልጉ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፆች፣ የውክልና መስጫ ቅፆች፣ የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ከየአገልግሎቱ ዓይነት ጋር ተያይዘው ይገኛሉ፡፡
- በአካል መምጣት የማይችሉ ወይም የማይገባዎት ከሆነና የአገልግሎት ጥያቄዎትን በፖስታ ቤት በኩል ከላኩ አገልግሎቱ ከሶስት ቀን እስከ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሊፈጅ ይችላል፡፡
- ማመልከቻውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ቴምብር የተለጠፈበትና የላኪ አድራሻ በትክክል የተፃፈበት መልሶ መላኪያ ፖስታ መላክ ይኖርብዎታል፡፡
Commerzbank Berlin
Account No. – 2673978 IBAN: DE31 1004 0000 0267397800
BLZ –10040000 Swift Code (BIC): COBADEFFXXX
- ሚስዮኑ የኦንላይን የክፍያ አሰራር የጀመረ በመሆኑ ለፈጣን አገልግሎት የOnline Banking System መጠቀም ይችላሉ፡፡
- በምንሰጠው አገልግሎት ቅሬታና አስተያየት ካለዎት በድህረ-ገፃችን በተዘጋጀው የአስተያየት መስጫ ቅፅ ላይ በመሙላት እንዲያቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (ቅፁን ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)
ማሳሰቢያ፡–
እ.አ.አ ከ ፌብሯሪ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ከታሪፍ በላይ እና በስህተት ገቢ የተደረገ ገንዘብ ተመላሽ የማናደርግ መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።
1-ሰነድ አልባ
- የሚሰጥዎትን ፎርም ሲሞሉ ቢያንስ የሁለት የቅርብ ቤተስብ ስምና ስልክ ቁጥር እንዲሁም የእርስዎን የዚህ አገር ስልክ ቁጥር መሙላት፤
- የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
- አሻራ መስጠትና መፈረም
- 2 ፎቶ ግራፍ ማቅረብ፤
- ከኢሚግሬሽን ፓስፖርት ማውጣት እንደሚችሉ ሲፈቀድልዎ ለመላክ እንዲያመች የፓስፖርት ፎርም መሙላት፤
- 2 ፎቶግራፍ ማለትም ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ፤
- የአገልግሎት ክፍያ የለውም
2-ቀደሞ የነበራቸው ፓስፖርት ይፈለግልኝ ጥያቄ
- የተሰጠዎትን ፎርም መሙላት፤
- የቀድሞ ፓስፖርት ቁጥር ካለዎት ይግለፁ፤
- አሻራ መስጠትና መፈረም፤
- የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
- የአገልግሎት ክፍያ የለውም
3- ሰነድ አልባ አመልክተው ኢትዮጵያዊነታቸው ተጣርቶ ፓስፖርት እንዲያወጡ ለተፈቀደላቸው፤
- የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
- ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
- የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ
- 147 ዩሮ
4- የስም፤ የእድሜ እና የትውልድ ቦታ ለውጥ ኖሯቸው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለማውጣት ጥያቄ ለሚያቀርቡ፤
- የስም ለውጥ በፍርድ ቤትላደረጉ
- በፍርድ ቤት የተለወጠው ስም ሰነድ በውጭ ጉዳይ የተረጋገጠ መሆን አለበት፤
- የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
- የቀድሞ ፓስፖርት ኮፒ፤
- ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
- የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
- 343 ዩሮ
- የልደት ቀን ወይም የትውልድቦታ ለውጥ ላደረጉ
- የትውልድ ቦታና የልደት ቀን ቅያሪ ያደረጉበት የልደት ሰርተፍኬት በውጭ ጉዳይ ረጋገጠ፤
- የቀድሞ ፓስፖርት ኮፒ፤
- የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
- ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
- የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ
- 343 ዩሮ
5- ለልጆች የአዲስ ፖስፖርት ጥያቄ
- የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት እናት/አባት መፈረም፤
- የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ የአባት ወይም የእናት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ፤
- እናት ወይም አባት ልጃቸው የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲያወጡ ፈቃደኛ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የጽሁፍ ማመልከቻ
- የሕፃኑ የልደት ሰርተፍኬት ተተርጉሞ በኖታሪ እና በlandgericht /District Court/ የተረጋገጠ እና በኤምባሲው በክፍያ የሚረጋገጥ፤
- ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤ የእናት/አባት እና የሕፃኑ የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
- 147 ዩሮ
6- የቀደሞ የትውልድ መታወቂያ ቢጫ ካርድ ኖሯቸው አዲሱን ዲጂታል የትውልድ መታወቂያ በእድሳት ለሚጠይቁ
- ለእድሳት ቅጽ 3ትን መሙላት፤
- 3 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
- የቀደሞ የትውልድ መታወቂያ ኮፒ
- አሻራ ሰጥቶ መፈረም፤
- ዜግነት ያገኙበትን አገር ፓስፖርት ኮፒ እና የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
- ዶላር በእለቱ የዩሮ ምንዛሪ ተቀይሮ
7– ውክልና
8– ሰነድ ማረጋገጥ
- የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ትውልድ መታወቂያ ለያዙ፤ 60.76 ዩሮ
- የኢትዮጵያ ፖስፖርት ወይም የትውልድ መታወቂያ ለሌላቸው፤ 93.76ዩሮ
9– የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
- በእለቱ አገልግሎት ለሚያገኙት በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት የደጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል
- በእለቱ አገልግሎት ለሚያገኙት በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት የደጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል