በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በጀርመን ከደቡብ ሱዳን ም/ሚሲዮን መሪ አምባሳደር Gum Dominic Motiok Motiok ጋር ውይይት አደረጉ
ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሰዳን ሀገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እየተጠናከረ መሆኑን ጠቅሰው ፣ ሁለቱ ጎረቤታማ አገሮች በበርካታ ሁለትዮሽ ጉዳዮች እየተሳሰሩ እንደሆነና የበለጠ እየተጠናከረ እንደሆነ ተወያይተዋል፡፡
በትውውቅ ውይይቱ ወቅትም ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለውን የተጠናከረ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተወከሉባቸው አገራት በሚሰሩበት ጊዜም ከፍ እንዲል በሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጣይ በትብብር በሚሰሩባቸው የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።