ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከሙኒክ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አመራር አባላት ተወካዮች ጋር ተወያዩ
(ሰኔ 08 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ): በጀርመን ፌደራል ሪፕብሊክ፣ በቼክ ሪፕብሊክ፣ በፖላንድ ሪፕብሊክ እና በዩክሬይን(ተሾአሚ) የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በሙኒክ እና አከባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አመራር አባላት ተወካዮች ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ወቅትም በቀጣይ የሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ከዳያስፖራዉ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ መክረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በኤምባሲው አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዩን ፍላጎት ለማሟላት በሚያስችሉ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ኤምባሲው ወደ ተለያዩ ከተሞች በመሄድ ለሚሰጠዉ አገልግሎት የዳያስፖራ አመራር አባላት ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ወደ ፊት ለሚያከናዉኗቸዉ የጋራ ዕቅድ አዉጥተዋል።