በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የበርሊን ኤምባሲ የሚሰጥ የቆንስላ አገልግሎት

መግቢያ

 •  በአካል መምጣት የማይችሉ ወይም የማይገባዎት ከሆነና የአገልግሎት ጥያቄዎትን በፖስታ ቤት በኩል ከላኩ አገልግሎቱ ከሶስት ቀን እስከ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሊፈጅ ይችላል፡፡
 • ማመልከቻውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ቴምብር የተለጠፈበትና የላኪ አድራሻ በትክክል የተፃፈበት መልሶ መላኪያ ፖስታ መላክ ይኖርብዎታል፡፡

Commerzbank  Berlin

Account No. –  2673978          IBAN:   DE31 1004 0000 0267397800

BLZ –10040000                      Swift Code (BIC): COBADEFFXXX

 • ሚስዮኑ የኦንላይን የክፍያ አሰራር የጀመረ በመሆኑ ለፈጣን አገልግሎት የOnline Banking System መጠቀም ይችላሉ፡፡
 • በምንሰጠው አገልግሎት ቅሬታና አስተያየት ካለዎት በድህረ-ገፃችን በተዘጋጀው የአስተያየት መስጫ ቅፅ ላይ በመሙላት እንዲያቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (ቅፁን ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

ማሳሰቢያ፡-
እ.አ.አ ከ ፌብሯሪ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ከታሪፍ በላይ እና በስህተት ገቢ የተደረገ ገንዘብ ተመላሽ የማናደርግ መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።

1-ፓስፖርት


በሚስዮኑ ሲዘጋጅ የነበረው ሰማያዊ ፓስፖርት ከአፕሪል 2015 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት የማይሰጥ በመሆኑ በምትኩ በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን በማሽን ተነባቢ ፓስፖርት እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2010 ጀምሮ ለኢትዮጵያውን እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በኢምባሲያችን በኩል አገር ቤት ተልኮ የሚዘጋጀው አዲሱ ፓስፖርት ለማግኘት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡

1.1 ለመጀመርያ ጊዜ ለአዲሱ በማሽን ተነባቢ ፓስፖርት ለማመልከት

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1.1.1 ለአዋቂ

– ከ1992 ዓ.ም በኋላ የተሰጠ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገር የወጡበት ስም ከነአያት ያለው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋናውን ቅጂ ከሁለት ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ (ሶስት ስም ወይም ስም  ከነአያት የሌለው ፓስፖርት ካለዎት የአያት ስም ያለው ሕጋዊ ሰነድ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡)

– የፓስፖርት መጠየቂያ ሁለት ቅፅ በመሙላት ማቅረብ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– በኤምባሲው ቆንስላ ክፍል በመገኘት አሻራ መስጠት (የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– መግቢያ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

– ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ መኖርያ ፈቃድ ማቅረብ

-የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ

1.1.2) በውጭ ሀገር ለተወለዱ ህፃናት

– የፓስፖርት መጠየቂያ ሁለት ቅፅ በመሙላት ማቅረብ(መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– የህፃን የልደት ምስክር ወረቀት

– ህፃኑ/ህፃኗ ፓስፖርት እንዲሰጠው/ እንዲሰጣት የአባትና የእናት ስምምነት ያለበት ማመልከቻ ማቅረብ

– የወላጆች ፓስፖርትና መኖሪድ ፈቃድ ኮፒ

– መግቢያ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

– የሌላ ሀገር ዜግነት የሌለው/ የሌላት መሆኑ/ኗ የሚያረጋግጥ ሰነድ

– የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)

1.2 አገልግሎቱ ያለቀ በማሽን ተነባቢ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማሳደስ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

– የፓስፖርት መጠየቂያ ሁለት ቅፅ በመሙላት ማቅረብ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– ሲጠቀሙበት የነበረው፣ አገልግሎቱ ያበቃ ፓስፖርት ኮፒ ማቅረብ

– የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ

– መግቢያ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

– የአገልግሎት ክፍያ – ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)                

1.3 በጠፋ ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

– ፓስፖርቱ ስለመጥፋቱ ለፖሊስ አመልክተው የተሰጠዎት ማስረጃ

– የፓስፖርት መጠየቂያ ሁለት ቅፅ በመሙላት ማቅረብ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– በኤምባሲው ቆንስላ ክፍል በመገኘት አሻራ መስጠት (የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– የጠፋውን ፓስፖርት ኮፒ ማቅረብ

– በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት

– መግቢያ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

– የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ

– የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)

2-የይለፍ ሰነድ/ ሊሴ-ፓሴ

በተለያየ ምክንያት ፓስፖርት ላልያዘ፣ ወደ ሀገሩ ለመመለስ ፈቃደኛ ለሆነ ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ ለአንድ ጊዜ ወይም ለመሄጃ ብቻ የሚያገለግል የጉዞ ሰነድ ነው፡፡

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

– በሁለት ቅጂ የሊሴ-ፓሴ መጠየቅያ ቅፅ መሙላት(መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

– የኢትዮጵያዊነት ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ

– መግቢያ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

– የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ

3- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ

በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ፣ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ከትውልድ ሀገራቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ፡-

 • ወደ ኢትዮጵያ ለመግባትና ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየትም ሆነ ለመኖር የመግቢያ ቪዛና የመኖርያ ፈቃድ እንዲኖረው አይጠየቅም፡
 • ከሀገር መከላከያ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ጉዳይ የመሳሰሉ የፖለቲካ መ/ቤቶች በስተቀር የስራ ፈቃድ እንዲያወጣ ሳይገደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ይችላል፡፡
 • እንደ ሀገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለገ በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግ መሰረት ለሀገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀዱ የኢንቨስትመንት መስኮች መሳተፍ ይችላል፡፡ ወዘተ

– የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ቤተሰቦች (የሌላ ሀገር ዜግነት ያለው ባል ወይም ሚስት ወይም ልጅ) የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ ሚስት/ባል/ልጅ መሆኑን ወይም መሆኗን የሚገልፅ የመታወቂ ካርድ የማግኘት ሙሉ መብት አለው፡፡

-የውጭ ሀገር ዜግነት የያዘ የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያውን የሚያገኘው የኢትዮጵያ ተወላጅ በመሆኑ ብቻ እንደ መብት ተቆጥሮ ሳይሆን አመልካቹ ለወገኖቹ የኑሮ መሻሻል ለትውልድ ሀገሩ እድገትና ብልፅግና የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ሲታመንበት ይሆናል፡፡

-የተወላጅነት መታወቂያ ለማግኘት የሚቀርቡ ከውጭ ሀገር የመነጩ የተለያዩ ማስረጃዎች (ከውጭ ሀገር የተሰጠ የልደት ምስክር ወረቀት፣ የጋብቻ ማስረጃ ወዘተ) በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተተረጎሙና ከዚያም ስለትክክለኛነታቸው በኤምባሲያችን የተረጋገጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3.1 አዲስ/ ለመጀመርያ ጊዜ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ለሚጠይቁ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

3.1.1- ዜግነት ከወሰደበት ሀገር የተሰጠና አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ማቅረብ፤

3.1.2- ከሚከተሉት አንዱን ስም ከነአያት የሚገልፅ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር የሰነድ ማስረጃ በተጨማሪ ማቅረብ፤

-የአመልካቹ አግባብ ባለው አካል የተሰጠና የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፣ ወይም፤

-የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ወይም ዋናው ፓስፖርት ለሌላቸው የፓስፖርት ቅጂያቸውን፣ ወይም፤

-ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ ወላጆች (biological) የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፣ ወይም፤

-ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ፣ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፣ ወይም፤

-ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ፣ ወይም፤

-ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ፣

3.1.3- መግቢያ ላይ በተጠቀሰው የፎቶግራፍ መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

3.1.4 በኤምባሲው የቆንስላ ክፍል በመገኘት አሻራ መስጠት (የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.1.5 የአገልግሎት ክፍያ- ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)

3.1.6 በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.2) አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች ስለሚሰጥ አገልግሎት በወላጅ አማካይነት መታወቂያውን ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

3.2.1 የወላጅ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ፤

3.2.2የወላጅ የፀና ፓስፖርት፣ ፓስፖርቱ የአያት ስም ከሌለው የወላጅ ስም ከነአያት የሚያረጋግጥ በተራ ቁጥር 3.1.2 ከተጠቀሱት አንዱን ማቅረብ

3.2.3 በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.2.4- የልጁ የተረጋገጠ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም ከላይ በተራ ቁጥር 3.1.2  ከተመለከቱት ማስረጃዎች አንዱን፤

3.2.5- የልጁ አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ፓስፖርት፤

3.2.6- የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)                      

3.2.7- መግቢያ ላይ በተጠቀሰው የፎቶግራፍ መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ

3.2.8 ዕድሜያቸው 14 እና ከዚያ በላይ የሆነ አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች በኤምባሲው በመገኘት አሻራ መስጠት

3.3- ለኢትዮጵያ ተወላጅ ለትዳር ጓደኛ ስለሚሰጥ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

3.3.1- ቢያንስ ለስድስት ወር የፀና ፓስፖርት (በአንዳንድ አገሮች ሁለት ስም ስለሚገለፅ ይህንኑ ተቀብሎ ማስተናገድ ይቻላል)

3.3.2- ቢያንስ ሁለት ዓመት የሆነው የተረጋገጠ የጋብቻ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅ ጋር፤

3.3.3- የባል/የሚስት የኢትዮጵያዊ ተወላጅነት መታወቂያ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፤

3.3.4- የትዳር ጓደኛ በመግቢያ ላይ በተጠቀሰው የፎቶግራፍ መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

3.3.5- መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ ፀንቶ ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሐላ ሰነድ አያይዞ ማቅረብ፤ ( ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.3.6- በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት፤ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.3.7- የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)

3.4 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂ ካርድ እድሳት

3.4.1- ዜግነት ካገኙበት አገር የተሰጠ ቢያንስ ለስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ዋናው ከሁለት ቅጂዎች ጋር

3.4.2- ቀደም ሲል የተሰጠ የአገልግሎት ዘመኑ ያለቀ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር

3.4.3- መግቢያ ላይ በተጠቀሰው የፎቶግራፍ መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ

3.4.4- የእድሳት ማመልከቻ በሁለት ቅጂ በመሙላት ማቅረብ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.4.5 በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የእድሳት ጥያቄ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ አያይዞ ማቅረብ (ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ) እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂ ካርድ ከሁለት ቅጂዎች ጋር አያይዞ ማቅረብ፤

3.4.6- የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)                    

3.4.7- መታወቂያው ከስድስት ወራት በላይ ሳይታደስ ከቆየ መታወቂያ ካርዱ እንደተመለሰ ተቆጥሮ በአዋጁ ያገኛቸው መብቶች በሙሉ ቀሪ ይሆናሉ፡፡ ከስድስት ወራት በላይ ሳያሳድሱ የቆዩበት አሳማኝ ምክንያት ለሚስዮኑ መሪ የማቅረብ መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከስድስት ወራት በታች ሳያሳድሱ የቆዩ ከዚህ በታች የተዘረዘረው የቅጣት ተመን በመክፈል መታወቂያ ካርዳቸውን ማሳደስ ይችላሉ፡፡ ከ1 ቀን እስከ 15 ቀን ያሳለፉ ለያንዳንዱ ቀን 3 የአሜሪካን ዶላር፣ ከ15 ቀን እስከ 30 ቀን ያሳለፉ የ15 ቀኑ የ45 ዶላር ቅጣት ላይ ለያንዳንዱ ቀን በ5 ዶላር ስሌት የሚደመርበት ይሆናል፡፡ ከ30 ቀን በላይ ያሳለፉ ከመጀመርያው ቀን ጀምሮ በ5 ዶላር ሂሳብ ስሌት ተባዝቶ የሚቀጡ ይሆናሉ፡፡

 3.5 የጠፋ ወይም የተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ስለመተካት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

3.5.1- መጥፋቱን ያመለከቱበት ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ

3.5.2- በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት፤ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.5.3- የጠፋው ወይም የተበላሸው መታወቂያ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ በሁለት ቅጂ (ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ) እንዲሁም የባለቤትዎ የኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ከሁለት ቅጂ ጋር አያይዞ ማቅረብ፤      

3.5.4- የጠፋው ወይም የተበላሸው መታወቂያ ካርድ በተራ ቁጥር 3.2 መሰረት የተሰጠ ከሆነ አገልግሎቱ የፀና የወላጅ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር አያይዞ ማቅረብ፤

3.5.5- የጠፋው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ መረጃው ለኢሚግሬሽን ተልኮ ሲታገድ፤

3.5.6- አሻራ ያልሰጡ እድሚያቸው 14 ዓመት በላይ የሆናቸው አመልካቾች አሻራ ሲሰጡ፤

3.5.7- የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)                      

3.5.8- መግቢያ ላይ በተጠቀሰው የፎቶግራፍ መስፈርት መሰረት 4 ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ቅረብ፤

3.6 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ እርማት

3.6.1- በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት፤ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

3.6.2-እርማት የሚደረገው የመታወቂያ ካርዱ ባለቤት የሚፈልገውን እርማት ጠቅሶ ሲያመለክትና እርማቱን ማድረግ ስለማስፈለጉ አሳማኝ ምክንያት በበቂ ማስረጃ በማስደገፍ ማቅረብ

3.6.3- እርማቱ የስም ለውጥ ከሆነ ስልጣን ከተሰጠው ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር፣ ወይም በጋብቻ ምክንያት የስም ለውጥ ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የጋብቻ ማስረጃ ፣ እንዲሁም የስም ለውጥ በጉዲፈቻነት ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ሕጋዊ የሰነድ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር ማቅረብ

3.6.4- እርማቱ የተጠየቀው በጋብቻ ምክንያት በተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ የመታወቂያ ካርድ ላይ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ ሁለት ቅጂ (ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)፣ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ፤

3.6.5- አሻራ ያልሰጡ እድሚያቸው 14 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው አመልካቾች አሻራ ሲሰጡ፤

3.7 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት የጊዜ ገደብና የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት

3.7.1- የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሚስዮን ሲቀርብ ሚስዮኑ ማመልከቻውን ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር ተሟልተው ከቀረበለት ጊዜ ጀምሮ በአስራ አምስት (15) የስራ ቀናት ውስጥ ለኢሚግሬሽን ይልካል፤

3.7.2- አመልካቹ መታወቂያው በአስቸኳይ እንዲዘጋጅለት ከጠየቀ በራሱ ወጭ ሚስዮኑ በፈጣን መልእክት መረጃውን በፖስታ አሽጎ ይልክለታል፤

3.7.3- ኢሚግሬሽን ያልተሟሉ መረጃዎች ሲደርሱት ሚስዮኑ መረጃዎችን አሟልቶ እንዲልክ ጥያቄው በደረሰው በአምስት (5) የስራ ቀናት ውስጥ ለሚስዮኑ ምላሽ ይልካል፤

3.7.4- ከሚስዮኑ የተሟላ ማስረጃ ለቀረበላቸው አመልካቾች ኢሚግሬሽን የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርዱንአዘጋጅቶ በአስር (10) የስራ ቀናት ወስጥ ለሚስዮኑ ይልካል፤

3.7.5 በተመሳሳይ ሁኔታ ሚስዮኑ የደረሰውን የአመልካቾች መታወቂያ ካርድ በሰባት (7) የስራ ቀናት ውስጥ ለጠያቂው እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

3.7.6- ሚስዮኑ ወይም ኢሚግሬሽን ማመልከቻ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ የመታወቂያ ካርዱ ለአመልካቹ ሊሰጠው እንደሚገባ ወይም እንደማይገባ መወሰን ይኖርበታል፡፡ የመታወቂያ ካርዱ እንዳይሰጥ የሚወሰን ከሆነ ምክንያቱ ለአመልካቹ በፅሁፍ ሊገለፅ ይገባል፡፡

3.7.7 አመልካቹ በተራ ቁጥር 3.7.6 በተሰጠው ወሳኔ ቅሬታ ካለው እስከ ሚስዮኑ መሪ ወይም ኢሚግሬሽን ዳይሬክተር ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፤

3.7.8-በተራ ቁጥር 3.7.7 በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አመልካች በፅሑፍ የሚያቀርበውን ቅሬታ ሚስዮኑ ተቀብሎ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ኢሚግሬሽን ተቀብሎ ለብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ይልክለታል ወይም በራሱ በኩል በቀጥታ ለተቋማቱ ያቀርባል፡፡

4- የውክልና አገልግሎት


በሀገር ቤት የሚኖርዎትን የንብረትና የዶክመንት ጉዳይ በሀገር ቤት በሚገኝ ሰው በውክልና  ለማስፈፀም ውክልና መስጠት ይችላሉ፡፡

– ውክልና ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል ፊት በመገኘት ለሶስተኛ ወገን በፊርማዎ  የሚሰጥ ኃላፊነት በመሆኑ በአካል ወደ ኤምባሲ የቆንስላ ክፍል መምጣትን የግድ ይላል፡፡ በመሆኑም የውክልና አገልግሎት በስልክ፣ በኢሜይል ወይም በደብዳቤ አይሰጥም፡፡

– ለናሙና የተዘጋጁ የውክልና መስጫ ቅፆች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

4.1- በኤምባሲው በተዘጋጀ የውክልና መስጫ ቅፅ መሰረት ወይም በራስዎ የተዘጋጀ የሚፈለገውን የውክልና ዓይነት ዝርዝር በሁለት ቅጂ ማቅረብ፡፡

4.2- የኢትዮጵያዊ ተወላጅነት ማረጋገጫ ሰነድ (የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ  ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወዘተ) ማቅረብ፡፡

4.3- የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ከዚህ ይጫኑ)

ማሳሰቢያ
ለውክልና ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝና የአመልካች ፓስፖርት ኮፒ ለተወካይ መላክ ይኖርብዎታል፡፡ከ ጥሮ ሳይሆን አመልካቹ ለወገኖቹ የኑሮ መሻሻል

5- ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት

– ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ወይም ከጀርመን፣ ፖላንድ፣ ቼክና ስሎቫክ የመነጩ የተለያዩ ሰነዶች (የትምህርት ማስረጃ፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ/የፍቺ/ ያላገቡ ማስረጃ፣ የንግድ ስምምነት ወዘተ) ትክክለኛነት የማረጋገጥ አገልግሎት ነው፡፡

– ከሀገር ቤት የመነጩ ሰነዶች በቅድሚያ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከውጭ የመነጩ ሰነዶች ደግሞ ከጀርመን ከሆነ በቅድሚያ ሰነዱን በPublic Notary እና District Court፤ ከፖላንድ፣ ቼክና ስሎቫክ ከሆነ ደግሞ በየሀገሩ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

5.1- እንዲረጋገጥ የሚፈለገው ኦሪጅናል ሰነድና የሰነዱ ቅጅ ከማመልከቻ ጋር አያይዞ ማቅረብ፡፡

5.2- የአመልካች ፓስፖርት (የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ) እና የመኖርያ ፈቃድ ኮፒ፡፡

5.3 -የአገልግሎት ክፍያ- ለማወቅ   ከዚህ ይጫኑ             

6- በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ 


በኢት/ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በውጭ የኢት/ ኤምባሲዎች በቆንስላዎች አገልግሎት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት መመዝገብ እንዲችል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት ወሳኝ ኩነት ለመመዝገብ የምዝገባ አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 7/2010 ሥራ ላይ ውሏል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ በበርሊንና አካባቢ እንዲሁም ኤምባሲው የሚሸፍናቸው ቼክ ሪፑብሊክ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫክያና ዩክሬን የምትኖሩ ኢትጵያውያን የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺና የሞት ወሳኝ ኩነቶችን በኤምባሲያችን አማካይነት ማስመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ ከታች የተገለጹትን መስፈርቶች አንብባችሁ ማሟላታችሁን ካረጋገጣችሁ consulberlin.eth@t-online.de  ወይንም aschalew.kebede@mfa.gov.et ላይ ስማችሁንና የምትመዘገቡትን የወሳኝ ኩነት ዓይነት በመግለጽ ቀጠሮ ማስያዝ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሳቢያ፡-አሁን የተጀመረው ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከዚህ በፊት የተከሰቱትን ኩነቶች አይመለከትም፡፡ ሙሉ መረጃውን ከዚህ በታች የተገለፀውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡:

 1. የልደትምዝገባ

በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ- ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች

ቅድመ-ሁኔታዎች

 1. በሚሲዮኑ የልደት ወሳኝ ኩነት ለማስመዝገብ የሕፃኑ ወላጆች አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ልደት የሚመዘገበው በሕይወት ለተወለደ ወይንም በሕይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፡፡
 3. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ምዝገባ አገልግሎት ፈላጊ ልደቱን ራሱ ማስመዝገብ አለበት፡፡
 4. 18 ዓመት ሳይሞላቸው ልጅ የወለዱ ወላጆች የልጃቸውን ልደት ለማስመዝገብ ሲቀርቡ ከሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ አስተዳደር ማንነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
 5. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ተመዝጋቢ ወላጆቹን በሚመለከት ቦታ ላይ መረጃውን ካስሞላ በኃላ የወላጅ ፊርማ ቦታ ላይ ሰረዝ (-) ምልክት በማድረግ ይታለፋል፡፡

ደጋፊ ማስረጃዎች

 1. ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡
 2. የሕፃኑ አሳደሪ ወይም ተንከባካቢ ልጁን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የአስዳሪነት ወይም የተንከባካቢነት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. የልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት
 1. የጋብቻ ምዝገባ

ድመ-ሁኔታዎች

 1. ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈጻም ማስባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈጸም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለቆንስላ አገልግሎት ክብር መዝገብ ሹም ማስታወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የሚፈጻም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
 2. የቆንስላው የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግሥቱ ጋብቻው የሚፈጻምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል ወይም በሚሲዮኑ ዌብ ፔጅ ላይ ያሳውቃል፡፡
 3. ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጋብቻ መቃወሚያ በጽሑፍመቅረብአለበት፤መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችሉ ወላጆችና ተወላጆች፣አቃቤ ሕግ፣ አሳዳሪ ወይም የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚልሰው መሆን አለበት።
 4. የክብር መዝገብ ሹሙ በቀረበው የጋብቻ መቃወሚያ ላይ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ማሳወቅ አለበት፡፡
 5. ወንድም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም አይችለም።
 6. ጋብቻ ህግ በሚከለክላቸው የሥጋና የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
 7. ተጋቢዎች በፍርድ ቤት እንዳያገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ የተገኘ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹሙ ጋብቻውን አይመዘገብም፡፡
 8. ማንኛውም ጋብቻ በፌዴራል ወይንም የቤተሰብ ሕግ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
 9. በባህል መሠረት የሚፈጻም ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይንም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሠረት የተፈጻመ መሆን አለበት፡፡
 10. አንዲት ሴት በብቸኝነት ለመኖር በህግ የተወሰነው ጊዜ ሳያልፍ ከሌላ ወንድ ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
 11. የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
 12. በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡

ደጋፊ ማስረጃዎች

 1. ጋብቻው የሚፈጻመው በሚኖሩበት አካባቢ ከሆነ የነዋሪነት ማስረጃ የተሰጠ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡
 2. የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
 3. ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለመቅረብ አለበት፡፡
 4. ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የሞተችበት/ባት ከሆነ የሞት ምስክር ወረቀት ካለመቅረብ አለበት፡፡
 5. ከ6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት 3 በ 4 ሳ.ሜ የሆነ የተጋቢዎች ፎቶግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
 6. በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ሥርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
 7. የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡

 

 • የፍቺ ምዝገባ

ቅድመ-ሁኔታዎች

 1. የተፋቺዎች መረጃ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ ላይ ተወስዶ ይመዘገባል፤ሆኖም ያልተሟላ መረጃ ሲኖር አስመዝጋቢዎች በተለያየ ጊዜ ቢመጡም ተጠይቆ ይሞላል፡፡

ደጋፊ ማስረጃዎች

 1. ፍቺው ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልጽ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
 2. ፍቺው የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ የፍቺ ልዩ ውክልና ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
 3. ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ ከሆነ የተሰጠው የጋብቻ ምስክር ወረቀት መመለስ አለበት፡፡
 1. የሞት ምዝገባ

ደጋፊ-ማስረጃዎች

 1. የሟች የነዋሪነት ወይም የመኖሪያ መታወቂያ ወይንም ፓስፖርት ወይንም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ወይንም የመኖሪያ ፍቃድ ካለመቅረብ አለበት፡፡
 2. አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለለፈበት ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂ ያማቅረብ አለበት፡፡
 3. ሞቱን የሚያስመዝግበው ፖሊስ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ/ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
 4. ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰብ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ መቅረብ አለበት፡፡
 5. የጊዜ ገደቡ ላለፈ የሞት ምዝገባ ስለሞቱ መከሰት የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
 6. ሞቱ የተከሰተው በውጭ አገር ዜጋ ላይ ከሆ ነከ ጤና ተቋም የተሰጠ የሞት ማሳወቂያ ወረቀት ወይም ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡