
News

ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በርሊን አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኤምባሲው ባልደረቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በጀርመን ቆይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል እና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለመደገፍ አበክረው እንደሚሰሩ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ ከሚሲዮኑ ሠራተኞች ጋር በነበራቸው የትውውቅ ውይይት ወቅት ገልጸዋል::
የሚሲዮኑ ባልደረቦችም ክቡር አምባሳደሩ በሚያደጓቸው ለስራ እንቅስቃሴዎች መሳካት በበለጠ ተነሳሽነትና የሀገር ፍቅር ከጎናቸው እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል::

Statement on the “Resolution” of the League of Arab States Regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) #Ethiopia
Statement on the “Resolution” of the League of Arab States Regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) #Ethiopia


የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ Twin Cities World Tourim Forum ፎረም ላይ ተሳተፉ
የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በጀርመን በርሊን እ.ኤ.አ ማርች 6,2023 በተካሄደዉ Twin Cities World Tourim Forum ላይ ተሳትፈዋል ።
ፎረሙ በየዓመቱ ከITB Berlin 2023 ኤግዚብሺን አንድ ቀን በፊት የሚዘጋጅ ሲሆን የቱሪዝም ከተማ መዳረሻዎች ትስስር በመፍጠር የተረጋጋ ቱሪዝም እንዲኖር ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ ነው ።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች ያሏት ሀገር መሆኗንና በዘርፋ እያከናወነች ያለውን ተግባራት በመድረኩ አጋርተዋል ።
በተጨማሪም የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና የቱሪዝም ሀላፊዎች ጋር የከተሞች ትስስር በመፍጠር ቱሪዝም ላይ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል ።