Consular Services

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የበርሊን ኤምባሲ የሚሰጥ የቆንስላ አገልግሎት

መግቢያ

  • ባለጉዳዮች ወደ በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኮንሱላር አገልግሎት በምትመጡበት ወቅት የተሟላ ሰነድ እና በቂ የሰነድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳወቅን ፣ ይህን በማሟላት ከመጣችሁ በኋላ ኮፒ ፍለጋ ላለመንከራተት እንዲሁም ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል፡፡

  • እንዲሁም መረጃዎቻችሁን በፖስታ የምትልኩ ባለጉዳዮች መረጃችሁን ወደ እናንተ መልሰን የምንልከው የመመለሻ ፖስታ ጨምራችሁ በምትልኩ ጊዜ ብቻ መሆኑን እናሳውቃልን፡፡

  • ከፌቡራሪ 2023 ጀምሮ የወጣው አዲስ የኮንሱላር አገልግሎት የዋጋ ታሪፍ

  • በሚስዮኑ የቆንስላ ክፍል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ ዋና ዋና የአገልግሎት ዓይነት ሰነድ አልባ፣ቀድሞ የነበራቸውን ፓስፖርት ይፈለግልኝ ፣ የድጋፍ ደብዳቤ ፣ የሰነድ ማረጋገጥና የውክልና አገልግሎት ናቸው፡፡
  • ከላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልግ ፎቶግራፍ ስፋቱ 3 x 4 ሴ.ሜ የሆነ፣ የሰውነት ክፍል በመቀስ ያልተነካ (ባዮሜትሪክ) ፣ ከስድስት ወር ወዲህ በከለር የተነሱት፣ ሁለቱ ጀሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለ፣ ከጀርባው ስም የተፃፈበት 4 ፎቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
  • ለፓስፖርትና ለትውልድ ኢትዮጵያዊ የሚያስፈልግ አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲው መምጣት የማይችሉ የቼክ፣ ስሎቫክና ፖላንድ ነዋሪዎች በአካባቢዎ ለሚገኝ ፖሊስ አሻራውን በመስጠት በፓብሊክ ኖታሪና በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በማረጋገጥ መላክ ይኖርበታል፡
  •  ከዚህ ቀደም አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
  • እድሜአቸው ከ 14 አመት በታች የሆኑ ህፃናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡
  •  አገልግሎቱን ለመውሰድ የሚያስፈልጉ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፆች፣ የውክልና መስጫ ቅፆች፣ የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ከየአገልግሎቱ ዓይነት ጋር ተያይዘው ይገኛሉ፡፡
  •  በአካል መምጣት የማይችሉ ወይም የማይገባዎት ከሆነና የአገልግሎት ጥያቄዎትን በፖስታ ቤት በኩል ከላኩ አገልግሎቱ ከሶስት ቀን እስከ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሊፈጅ ይችላል፡፡
  • ማመልከቻውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ቴምብር የተለጠፈበትና የላኪ አድራሻ በትክክል የተፃፈበት መልሶ መላኪያ ፖስታ መላክ ይኖርብዎታል፡፡

Commerzbank  Berlin

Account No. – 2673978          IBAN:   DE31 1004 0000 0267397800

BLZ –10040000                      Swift Code (BIC): COBADEFFXXX

  • ሚስዮኑ የኦንላይን የክፍያ አሰራር የጀመረ በመሆኑ ለፈጣን አገልግሎት የOnline Banking System መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • በምንሰጠው አገልግሎት ቅሬታና አስተያየት ካለዎት በድህረ-ገፃችን በተዘጋጀው የአስተያየት መስጫ ቅፅ ላይ በመሙላት እንዲያቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (ቅፁን ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

ማሳሰቢያ፡
.. ፌብሯሪ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ከታሪፍ በላይ እና በስህተት ገቢ የተደረገ ገንዘብ ተመላሽ የማናደርግ መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።

 

1-ሰነድ አልባ


  • የሚሰጥዎትን ፎርም ሲሞሉ ቢያንስ የሁለት የቅርብ ቤተስብ ስምና ስልክ ቁጥር እንዲሁም የእርስዎን የዚህ አገር ስልክ ቁጥር መሙላት፤
  • የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
  • አሻራ መስጠትና መፈረም
  • 2 ፎቶ ግራፍ ማቅረብ፤
  • ከኢሚግሬሽን ፓስፖርት ማውጣት እንደሚችሉ ሲፈቀድልዎ ለመላክ እንዲያመች የፓስፖርት ፎርም መሙላት፤
  • 2 ፎቶግራፍ ማለትም ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ፤
  • የአገልግሎት ክፍያ የለውም

2-ቀደሞ የነበራቸው ፓስፖርት ይፈለግልኝ ጥያቄ

 

  • የተሰጠዎትን ፎርም መሙላት፤
  • የቀድሞ ፓስፖርት ቁጥር ካለዎት ይግለፁ፤
  • አሻራ መስጠትና መፈረም፤
  • የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
  • የአገልግሎት ክፍያ የለውም

 

3- ሰነድ አልባ አመልክተው ኢትዮጵያዊነታቸው ተጣርቶ ፓስፖርት እንዲያወጡ ለተፈቀደላቸው፤

 

  • የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
  • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
  • የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ
  • 147 ዩሮ

 

4- የስም፤ የእድሜ እና የትውልድ ቦታ ለውጥ ኖሯቸው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለማውጣት ጥያቄ ለሚያቀርቡ፤

 

  • የስም ለውጥ በፍርድ ቤትላደረጉ
  • በፍርድ ቤት የተለወጠው ስም ሰነድ በውጭ ጉዳይ የተረጋገጠ መሆን አለበት፤
  • የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
  • የቀድሞ ፓስፖርት ኮፒ፤
  • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
  • የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
  • 343 ዩሮ
    • የልደት ቀን ወይም የትውልድቦታ ለውጥ ላደረጉ
  • የትውልድ ቦታና የልደት ቀን ቅያሪ ያደረጉበት የልደት ሰርተፍኬት በውጭ ጉዳይ ረጋገጠ፤
  • የቀድሞ ፓስፖርት ኮፒ፤
  • የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት መፈረም፤
  • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
  • የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ
  • 343 ዩሮ

5- ለልጆች የአዲስ ፖስፖርት ጥያቄ

  • የፓስፖርት ፎርም በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመሙላት እናት/አባት መፈረም፤
  • የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ የአባት ወይም የእናት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ፤
  • እናት ወይም አባት ልጃቸው የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲያወጡ ፈቃደኛ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የጽሁፍ ማመልከቻ
  • የሕፃኑ የልደት ሰርተፍኬት ተተርጉሞ በኖታሪ እና በlandgericht /District Court/ የተረጋገጠ እና በኤምባሲው በክፍያ የሚረጋገጥ፤
  • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤ የእናት/አባት እና የሕፃኑ የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፤
  • 147 ዩሮ

6- የቀደሞ የትውልድ መታወቂያ ቢጫ ካርድ ኖሯቸው አዲሱን ዲጂታል የትውልድ መታወቂያ በእድሳት ለሚጠይቁ

 

  • ለእድሳት ቅጽ 3ትን መሙላት፤
  • 3 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሁለት ጆሮ በትክክል የሚታይ እና ጀርባው ነጭ የሆነ፤
  • የቀደሞ የትውልድ መታወቂያ ኮፒ
  • አሻራ ሰጥቶ መፈረም፤
  • ዜግነት ያገኙበትን አገር ፓስፖርት ኮፒ እና የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
  • ዶላር በእለቱ የዩሮ ምንዛሪ ተቀይሮ

 

7– ውክልና

 

8– ሰነድ ማረጋገጥ

 

  • የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ትውልድ መታወቂያ ለያዙ፤ 60.76  ዩሮ
  • የኢትዮጵያ ፖስፖርት ወይም የትውልድ መታወቂያ ለሌላቸው፤ 93.76ዩሮ

9– የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት

 

  • በእለቱ አገልግሎት ለሚያገኙት በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት የደጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል
  • በእለቱ አገልግሎት ለሚያገኙት በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት የደጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል