Civil Registration

The Embassy provides Civil Registration – Birth Certificate, Marriage Certificate, Death Certificate and Divorce Certificate services to Ethiopian citizens residing in Germany and covering countries.

የምንሰጣቸው የሲቪል ምዝገባ አገልግሎቶች

የልደት ምዝገባ አገልግሎት
  • ልደትን ለማስመዝገብ አስመዝጋቢው ሚሲዮኑ ወይም ኢምባሲው በሚገኝበት ሀገር መደበኛ ነዋሪ መሆን አለበት፡፡
  • በውጭ አገር የተከሰተ ልደትን ለማስመዝገብ የህፃኑ ወላጆች ወይም ከወላጆች አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆን አለባቸው
  • የኢትዮጵያ ወይም ኢምባሲ ባለበትና በሚያካልለው አገር የሚኖር ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ዉጭ ሀገር ያለ ኢትዮጲያዊ ወይም ትውልድ ኢትየጵያዊ በአካል በመቅረብ ብቻ ልደቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
  • ልደት የሚመዘገበው በህይወት ለተወለደ ወይም በሕይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፡፡
  • አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ መታወቂያ ወይም ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም በአገሩ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተሰጠ መታወቂያ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  • በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  • በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልደቱ የተከሰተው ከጤና ተቋም ውጭ ከሆነ አስመዝጋቢው ካዋለደው አካል የተሰጠ የልደት ማሳወቂያ ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
  • የህጻኑ አሳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ወይም ሞግዚት ልደቱን ለማስመዝገብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ እና በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ ሕጋዊ የአሳዳሪነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ዘግይተውና የምዝገባ ጊዜውን አሳልፈው ለሚቀርቡ አስመዝጋቢዎች ምዝገባውን ሳያስመዝግቡ የቆዩበት ምክንያት የሚገልጽ በቂና ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለክብር መዝገብ ሹሙ ማስታወቅ አለባቸው፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
  • የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግስቱ ጋብቻው የሚፈፀምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና በባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን ይጨምራል፡፡
  • ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጋብቻ መቃወሚያ በጽሁፍ መቅረብ አለበት፤ መቃወሚያ ሊያቀርቡ የሚችሉ ወላጆችና ተወላጆች፣ አቃቤ ሕግ፣ አሳዳሪ ወይም የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚል ሰው መሆን አለበት፡፡
  • የክብር መዝገብ ሹሙ በቀረበው የጋብቻ መቃወሚያ ላይ በአምስት ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ማሳወቅ አለበት፡፡
  • ወንደም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞሊቸው ጋብቻ መፈፀም አይችለም፡፡
  • በቀጥታ የስጋ ዘመዳሞች (በወላጆችና በተወላጆች) መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነዉ፡፡
  • ወደጎን በሚቆጠር የስጋ ዝምድና አንድ ወንድ ከእህቱ ወይም ከአክስቱ እንዲሁም አንዲት ሴት ከወንድሟ ወይም ከአጎቷ ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነዉ፡፡
  • በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነዉ፡፡
  • ወደጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዝምድና ባል ከሚስቱ እህት ወይም ሚስት ከባሏ ወንድም ጋር ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነዉ፡፡
  • በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ ተራ ቁጥር 5 እስከ 9 ያለው ጋብቻው በሼርያ ፍርድ ቤት የተፈፀመ ከሆነ በፍርድ ቤቱ በተሰጠው ማሰረጃ መሰረት ጋብቻው የሚፈጸም ነው፡፡
  • ማንኛዉም ተጋቢ አስቀድሞ በጋብቻ የተሳሰረ ከሆነ ይሄዉ ጋብቻ ፀንቶ በቆየበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ አይመዘገብም፡፡
  • ጋብቻ ሲፈፀም ሁለቱም ተጋቢዎች በአካል ቀርበዉ ክብር መዝገብ ላይ መፈረም አለባቸዉ፡፡
  • ተጋቢዎች በፍርድ ቤት እንዳያገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ የተገኘ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹሙ ጋብቻውን አይመዘገብም፡፡
  • አንዲት ሴት በብቸኝነት ለመኖር በህግ የተወሰነው ጊዜ ካላለፈ በስተቀር እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
  • የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙለ ፍቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
  • በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ጋብቻው በሃይማኖታዊ ወይም በባህላዊ የተፈፀመ ከሆነ ሃይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ጋብቻውን ከፈፀመው አካል የተሰጠ ማስረጃ ላይ የምስክሮችን ስም በመውሰድ መመዝገብ ይቻላል፡፡
  • በሃይማኖታዊ ወይም በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ ማስረጃ የሚከተሉትን መያዝ አለበት (የተጋቢዎች ሙሉ ስም፣ ዕድሜ፣ መደበኛ መኖሪያ ቦታ፣ ጋብቻው የተፈፀመበት ቀን ወርና ዓመተምህረት፣ ጋብቻው ተፈፀመበት ቦታ፣ የምስከሮች ሙሉ ሰም መደበኛ መኖሪያ ቦታና ፊርማቸውን) የያዘ መሆን አለበት፡፡
  • በማንኛውም ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት፡፡
  • ማንኛውንም ጋብቻ ለማስመዝገባ ተጋቢወች ያላገባ ማስረጃ መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጋቢዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ከ 6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ-ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
  • የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
  • የክብር መዝገብ ሹሙ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች መሟላታቸውን በመጠየቅ ያረጋግጣል፡፡
  • ተጋቢዎችና ምስክሮቹ የመሃላ ቃል ከመስጠታቸው በፊት የሚሰጡት ቃል ስለሚያስከትለው ሃላፊነት የክብር መዝገብ ሹሙ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡፡
  • ተጋቢዎችና ምስክሮቹ ጋብቻ ለመፈጸም አስፈላጊ ሁኔታዎች አለመጣሳቸውን በጽሁፍ በሰፈረ ቃለ መሃላ ያረጋግጣሉ፡፡
  • የክብር መዝገብ ሹሙ ተጋቢዎቹ በህጋዊ ጋብቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን አስታውቆ ለተጋቢዎቹ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡
  •  
  • ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሆን አለበት፤
  • ፍቺው በተፋቺዎቹ በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ በሚኖርበት መደበኛ መኖሪያ ሀገር በሚገኝ ፍርድ ቤት የተፈጸመ መሆን አለበት፡፡
  • የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት፡፡
  • ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም በአገሩ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተሰጠ መታወቂያ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም የነዋሪነት ወይም በአገሩ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተሰጠ መታወቂያ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ እንደሆነ የጋብቻ ምስክር ወረቀት መመለስ አለበት፡፡
  •  
  • ሟች በአደጋ ምክንያት ከሞቱ ሰዎችና አደጋው ከደረሰባቸው ተጎጂዎች ጋር አብሮ የነበረ ሰው ሊገኝ አለመቻሉን ካጣራ አካል የተሰጠ ማስረጃ ሲቀርብ ሞቱ ይመዘገባል፡፡
  • ሟችን ለማስመዝገብ ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው፣ አብሮ ይኖር የነበረ ሰው የሌለ እንደሆነ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣ እነዚህ የሌሉ እንደሆነ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ሟች መሞቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
  • የሟች ማንነትን የሚገልጽ ማሰረጃ ወይም መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሞቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሞት አስመዝጋቢ ሞቱ ከተከሰተበት ሀገር ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የሞት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  • ዘግይተውና ጊዜ ገደቡን አሳልፈው ለሚቀርቡ አስመዝጋቢዎች ምዝገባውን ሳያስመዝግቡ የቆዩበት ምክንያት የሚገልጽ ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም አዲሱ የምዝገባ ስርዓት ከመጀመሩ በፊት የተከሰተን የሞት ምዝገባን አይጨምርም፡፡